Fana: At a Speed of Life!

የአሜሪካ መንግስት በኢትዮጵያ ላይ ለሚያደርገው ጣልቃ ገብነት ለመጠቀም ለአዲስ ስታንዳርድ የኦንላይን መፅሔት ቀጥታ የገንዘብ ድጋፍ እንደሚያደርግ ታወቀ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 10፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) አዲስ ስታንዳርድ በመባል የሚታወቀው የኦንላይን መፅሄት በዴሞክራሲ ማስፋፋት ስም በሀገራት የውስጥ ፖለቲካ በመግባት ከሚፈተፍተው የአሜሪካ “ኢንዶውመንት ፎሮ ዴሞክራሲ” ከተባለው የዩናይትድ ስቴትስ መንግስት ተቋም ቀጥታ የገንዘብ ድጋፍ እንደሚደረግለት የፋና ምንጭ ጠቆመ።
 
ፋና ብሮድካስቲንግ ኮሮፖሬት ያገኘው መረጃ እንደሚያመለክተው አዲስ ስታንዳርድ የኦንላይን መፅሄት በፈረንጆቹ 2019 ላይ ብቻ 75 ሺህ 990 የአሜሪካ ዶላር ከዚህ ድርጅት ተቀብሏል።
 
ይህንንም ገንዘብ በድርጅቱ በኩል የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት ሲሰጥ መቆየቱን መረጃው ያመለክታል።
 
የአሜሪካ መንግስት ቀጥታ በሚቆጣጠራቸው በእነዚህ ተቋማቱ በኩል ለመገናኛ ብዙሃን ገንዘብ በማቅረብ በሀገራት የውስጥ ፖለቲካ ውስጥ የሚፈተፍት ሲሆን፥ የዩናይትድ ስቴትስን ብሄራዊ ጥቅም ለማስጠበቅ ይሰራል።
 
አዲስ ስታንዳርድ ከአሜሪካ የውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት ይህን ያህል መጠን ያለው ገንዘብ መቀበሉም ዋሽንግተን የሚዲያ ተቋሙን በኢትዮጵያ ጉዳይ ተፅዕኖዋን ለማሳደር እና ፍላጎቷን ለማስፈፀም እየተጠቀመችበት ለመሆኑ ማሳያ መሆኑ ተመልክቷል።
 
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.