Fana: At a Speed of Life!

የኡጋንዳ ወጣቶች የአፍሪካን ችግር በአፍሪካዊ መፍትሄ የመፍታት ልምድ ማደግ እንዳለበት ገለፁ

አዲስ አበባ፣ ታህሰሳ 14፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በኡጋንዳ የኢትዮጵያ ኤምባሲ በኡጋንዳ ከሚገኘው የአፍሪካውያን ወጣቶች ካውከስ ጋር በመተባበር በኢትዮጵያ ያለውን ጦርነት በተመለከተ በኡጋንዳ ለሚገኙ ወጣቶች የግንዛቤ ማስጨበጫና የውይይት መድረክ በበይነ መረብ አካሂዷል፡፡

የአፍሪካውያን ወጣቶች ካውከስ ሊቀመንበር ዶክተር አንድሪው በመግቢያ ንግግሩ ድርጅቱ መንግስታዊ ያልሆነ፣ የአፍሪካ ወጣቶችን በዲፕሎማሲ መስክ አቅም ለማጎልበት እንደተቋቋመ በመግለፅ በኢትዮጵያ ያለውን ግጭት በተመለከተ ወጣቶች ትክክለኛ ግንዛቤ እንዲኖራቸው፣ በአህጉሪቱ ጉዳይ ያላቸውን ሀሳብ እና ጥያቄዎች በፓን-አፍሪካዊ ስሜት ለማንሸራሸር በማቀድ ከኤምባሲው ጋር በትብብር እንደተዘጋጀ ገልጿል።

በኡጋንዳ የኢትዮጵያ አምባሳደር ዓለምፀሀይ የህወሓት አሸባሪ ቡድን በኢትዮጵያ ላይ ጦርነት ለምን እንደከፈተ፣ መንግስት ተገዶ የገባበት መሆኑን፣ ያሉ ችግሮችን በሰላማዊ መንገድ እንዲፈታ ቀደም ሲል በህዝብና መንግስት የተደረጉ ጥረቶችን፣ አሸባሪ ቡድኑ ጦርነቱን ባስፋፋባቸው አጎራባች ክልሎች በህዝብና በንብረት ላይ ያደረሳቸውን መጠነ ሰፊ ውድመት፣ በአሁኑ ጊዜ ህወሓት ተሸንፎ በወረራ የያዛቸውን ቦታዎች እየለቀቀ መሆኑን ጠቅሰዋል።

ከዚህ ባለፈም ህወሓት ሀሰተኛ የፕሮፖጋንዳ ዘመቻ ላይ ግጭቱ ከጀመረ ጀምሮ መጠመዱን በዚህም ዓለም አቀፍ ሚዲያዎች እና አንዳንድ ምዕራባውያን አገራት ለህወሓት ወገንተኝነት ብሎም ጣልቃ-ገብነት ያሳዩበት እንደሆነ በዚህም ኢትዮጵያውያን እና አፍሪካውያን ወንድሞቻቸው የውጭ ጣልቃ-ገብነትን በመቃወም የበቃ እንቅስቃሴ በዓለም ዙሪያ እያካሄዱ እንደሚገኙ ገልጸዋል፡፡

በእለቱ በኢትዮጵያ ያለውን ጦርነት በተመለከተ ሀሳቡን ያካፈለው የህግ ባለሙያ ሚካኤል ብሌር ኢትዮጵያ በምስራቅ አፍሪካ ስትራቴጂካዊ ጠቀሚታዋ የጎላ ሀገር እንደሆነች በመግለፅ ÷ ጦርነቱ በቀጠናው ያሉ አገራትን ጭምር ተፅዕኖ ውስጥ ሊጨምር እንደሚችል ያለውን ስጋት ገልጿል፡፡

ኡጋንዳዊው የማህበረሰብ አንቂ ላምበርት ኢቢቱ በበኩሉ ÷ ወጣቶች የዓለምአቀፍ ሚዲያዎች የሚያስተጋቡትን ሀሰተኛ ዘገባዎች በጥንቃቄ እንዲመለከቱ እና ኢትዮጵያ ላይ ከውስጥ እና ከውጭ በቅንጅት የተከፈተባትን ጦርነት አፍሪካን የማንበርከክ እኩይ ሴራ እንደሆነ እና ይህም ሴራ በኢትዮጵያውያን አንድነት እየተቀለበሰ እንደሚገኝ ተናግሯል፡፡

እኛ አፍሪካውያን ከኢትዮጵያን ወንድሞቻችን ጎን መቆም ይገባናል በማለትም ጥሪውን አቅርቧል፡፡

በእለቱ በመድረኩ ተሳታፊ የሆኑት ወጣቶች በሰጡት አስተያየት አፍሪካ ለሚያጋጥሟት ችግሮች አፍሪካዊ መፍትሄዎችን የያዘ ማዕቀፍ በመተግበር ልምድን ማሳደግ ይገባል ማለታቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ጽህፈት ቤት መረጃ ያመላክታል።

አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.