Fana: At a Speed of Life!

የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር የአረንጓዴ ዐሻራ “አንድ ሰው 100 ችግኝ የመትከል መርሐ ግብርን” ጀመረ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 16፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር የአረንጓዴ ዐሻራ “አንድ ሰው 100 ችግኝ የመትከል መርሐ ግብርን” ጀምሯል፡፡
የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ፣ የስፔስ ሳይንስ እና ጂኦ ስፓሻል ኢንስቲትዩት አመራሮች እና ሠራተኞች በእንጦጦ የአፍሪካ የስፔስ ማዕከል ውስጥ ችግኝ ተክለዋል፡፡
የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዴኤታ ዶክተር ባይሳ በዳዳ በዚሁ ወቅት እንደገለጹት÷ በአረንጓዴ ዐሻራ መርሐ ግብር ችግኞችን ከመትከል በዘለለ የመንከባከብና ክትትል የማድረግ ሥራ ትኩረት ሊሰጠው ይገባል፡፡
የአረንጓዴ ዐሻራ የችግኝ ተከላ መርሐ ግብሩ በሌሎች ቦታዎች ተጠናክሮ እንደሚቀጥል የሚኒስቴሩ መረጃ አመላክቷል፡፡
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.