Fana: At a Speed of Life!

የኦሮሞ ህዝብን ወደ አዲስ ምዕራፍ ለማሻገር ዳግም ቃሌን አድሳለሁ – አቶ ሽመልስ አብዲሳ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 15፣ 2014(ኤፍ ቢ ሲ) የኦሮሞ ህዝብን ወደ አዲስ ምዕራፍ በማሻገር ለውጡን ለማስቀጠል ዳግም ቃሌን አድሳለሁ ሲሉ የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሽመልስ አብዲሳ አስታወቁ።
በጨፌ ኦሮሚያ በድጋሜ ርዕሰ መስተዳድር ሆነው ዛሬ የተሾሙት አቶ ሽመልስ ባደረጉት ንግግር በ2013 ዓ.ም ትላልቅ የፖለቲካና የኢኮኖሚ ስኬቶች መመዝገባቸውን ገልጸዋል።
በውስብስብ ችግር ውስጥ ሆነን ሀገራችንን ለማፍረስ የቋመጡ የውስጥና የውጭ ሃይሎችን ያሳፈረና ተስፋቸውን ያስቆረጠ ምርጫ በማካሄድ ዳግም ታሪክ ማደስ ችለናል ነው ያሉት።
ምርጫው ተሳክቶ ዛሬ ለደረስንበት ስኬት ላበቃን ህዝባችንንና ባለድርሻ አካላት ምስጋና ይገባቸዋል ብለዋል።
አሸባሪዎቹ ሸኔና ህወሃትን ማፅዳት የክልሉንም ሆነ የሀገሪቱ ሰላም አስተማማኝ ማድረግ ቀዳሚ ተግባራችን ነው ያሉት ርዕሰ መስተዳድ
የክልሉ ወጣቶች እኛ እያለን ሀገራችን አትፈርስም በማለት መከላከያና ልዩ ሃይሉን መቀላቀላቸውን አድንቀው ይሄው ድጋፍ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ተናግረዋል።
“ኦሮሞን ከኢትዮጵያዊ ማንነት ለማራቅና የተሸናፊነት አባዜ ውስጥ እንዲቆይ ያደረገውን አሸባሪ ሃይል አከርካሪውን በመስበር የበለፀገች አሮሚያና ኢትዮጵያን ለትውልድ እናስረክባለን” ነው ያሉት።
“በዚህም የማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ልማቶችን ሌት ተቀን እየተረባረብን አፋጣኝ ውጤት እናስመዘግባለን” ብለዋል።
“የጥንካሬያችን ማዕከል ኦሮሞነት ነው፣ ማንነታችን የበለፀገች፣ አንገቷን ቀና ያደረገች ኢትዮጵያን መፍጠር ነው” ሲሉ አቶ ሽመልስ አስታውቀዋል።
በተለይ የግብርና፣ የቴክኖሎጂና ሜካናይዜሽን አገልግሎት በማስፋት የአጠቃላይ ሰብል ልማትና የስንዴ መስኖ ልማት፣ የእንስሳት ሀብት፣ የአረንጓዴ ኢኮኖሚ ግንባታ ላይ በትኩረት ይሰራል ብለዋል።
የኑሮ ውድነት ማቃለል፣ትምህርት፣ ጤና፣የመንገድ ልማት፣ የከተሞች ሴክተር ልማትና ቀልጣፋ አገልግሎት መስጠት ልዩ ትኩረት የሚሰጠው ቀዳሚ ተግባር መሆኑንም አመላክተዋል።
የወጣቶችና ሴቶችን ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት ማረጋገጥ፣ ሌብነትና የመልካም አስተዳደር እጦት ችግርን ማቃላል የትኩረት አቅጣጫችን ነው ብለዋል።
ከአጎራባች ክልሎች ጋር ወንድማማችነትን ይበልጥ ለማጠናከር አብሮ መልማትና ማደግ ላይ በትብብር እንደሚሰራም ገልጸዋል።
ከዚህ በፊት በነበረው አካሄድ የህዝቡን ጥያቄ መመለስ እንደማይቻል አውስተው፤ አሁን የመጣውን ለውጥ በመጠቀም በገቢ አቅም ማሳደግ፣ የህዝቡ የማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ልማት ተሳትፎ ይበልጥ ማጠናከር አለብን ብለዋል።
የኦሮሞ ቄሮና ቀሬ አሸባሪውን ህወሃት በማስወገድ ዛሬ ለደረስንበት ደረጃ አብቅታችሁናል ያሉት
ርዕሰ መስተዳድአሁንም ትልቁ ጠላታችን የሆነውን ድህነት ማሸነፍ አለብን ብለዋል።
መላው የክልሉ ህዝብ፣ የኦሮሞ ምሁራን ለሁሉን አቀፍ ልማት በገንዘብ፣ ጉልበትና ዕውቀት ማገዝ እንደሚገባቸው አመልክተዋል።
የውስጥና ውጭ ጠላት ለመቅበር የኦሮሞ ህዝብ ከሌላው ኢትዮጵያዊ ጋር በመሆን ከመቼውም ጊዜ በላይ በአንድነት መቆም አለብን ነው ያሉት።
የክልሉ መንግስት ሠራተኞች ከመቼውም ጊዜ በላይ ጠንክረን መስራት አለብን፤ የዲያስፖራ አባላት የክልሉን ልማት በማገዝ ሀገራችንን በጋራ ሆነን ማሻገር አለብን ሲሉ አቶ ሽመልስ ማብራራታቸውን ኢዜአ ዘግቧል።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
0
People Reached
0
Engagements
Boost Post
Like

Comment
Share
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.