Fana: At a Speed of Life!

የከባድ ኩላሊት ህመም ምልክቶች

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 9፣ 2013(ኤፍ ቢሲ) የከባድ ኩላሊት ህመም ምልክቶች ምንድናቸው?
ለኩላሊት ህመም በርካታ ነገሮች ምክንያት መሆናቸው ይነገራል፡፡
ከዚህ በተጓዳኝ ደግሞ ህመሙ እንደቆየበት ደረጃ የተለያዩ የምልክት ደረጃዎች እንዳሉትም የህክምነናባለሙያዎች ያስረዳሉ፡፡
ከዚህ በታች የተጠቀሱት ምልክቶች ዋና ዋናዎቹ መሆናቸውንም ይገልጻሉ፡፡
እነሱም ደም ማነስ፣ ደም የተቀላቀለበት ሽንት፣የጠቆረ ሽንት፣ንቁ አለመሆን፣ የሽንት መጠን መቀነስ፣ የእግር፣ የእጅ እና የቁርጭምጭሚት ማበጥ፣የድካም ስሜት ፣ የደም ግፊት፣ እንቅልፍ እጦት የሚያሳክክ ቆዳ ናቸው፡፡
እንዲሁም የምግብ ፍላጎት መጥፋት፣ ወንዶች ላይ ብልትን ማስነሳት መቸገር፣በሌሊት ቶሎ ቶሎ ለሽንት መመላለስ፣ የትንፋሽ እጥረት፣ሽንት ላይ ፕሮቲን መገኘት በፍጥነት የሚቀያየር የሰውነት ክብደት እና ራስ ምታት መሆናቸው ይነገራል፡፡
በሌላ በኩል ሽንት ይዞ አለመቆየት ፣ በቂ ውሃ መጠጣት፣ጨው የበዛበት ምግብ አለመመገብ፣የአልኮል መጠጥ መጠን መቀነስ፣ሲጋራ አለማጨስና ሌሎች የኩላሊት ህመምን ለመከላከል ይረዳሉ፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡-https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.