Fana: At a Speed of Life!

የኮማንደር አሰልጣኝ ሁሴን ሽቦ “አዳኙ አሰልጣኝ” መጽሃፍ ተመረቀ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 7፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የኮማንደር አሰልጣኝ ሁሴን ሽቦ “አዳኙ አሰልጣኝ” መጽሃፍ በዛሬው እለት ተመርቋል።

በመጽሃፉ ምረቃ ላይም የኦሮሚያ ክልል ርእሰ መስተዳድር አቶ ሽመልስ አብዲሳ እና የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ተቀዳሚ ምክትል ፕሬዝዳንት ኮማንደር አትሌት ደራርቱ ቱሉን ጨምሮ የተለያዩ የመንግስት መስሪያ ቤቶች ኃላፊዎች ተገኝተዋል።

በተጨማሪም ታዋቂ አትሌቶች፣ ታዋቂ አሰልጣኞች፣ ማናጀሮች፣ አንጋፋ ባለድል አትሌቶች፣ ጥሪ የተደረገላቸው የአትሌቲክሱ ቤተሰቦች በመጽሃፍ ምረቃው ላይ መታደማቸውን ከኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

የኮማንደር አሰልጣኝ ሁሴን ሽቦ (አባቢያ)”አዳኙ አሰልጣኝ” በሚል ያሳተሙት መጽሃፍ በአትሌቲክሱ ፈርቀዳጅ ግለታሪክ መጽሐፍ መሆኑም ተነግሮለታል።

#FBC

የዜና ሰዓት ሳይጠብቁ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ትኩስ እና ሰበር ዜናዎችን በፍጥነት በአጭር የፅሁፍ መልዕክት መልክ በስልክዎ ላይ እንዲደርስዎ ወደ 8111 OK ብለው ይላኩ።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.