Fana: At a Speed of Life!

የወላይታ ሶዶና የሚዛን ቴፒ ዩኒቨርሲቲዎች በተለያዩ የትምህርት ዘርፎች ያስተማሯቸውን ተማሪዎች አስመረቁ

አዲስ አበባ፣ ጳጉሜን 3፣ 2012(ኤፍ.ቢ.ሲ) የወላይታ ሶዶ እና የሚዛን ቴፒ ዩኒቨርሲቲዎች በተለያዩ የትምህርት ዘርፎች በመጀመሪያና ሁለተኛ ድግሪ ያስተማሯቸውን ተማሪዎች አስመርቀዋል፡፡

የወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ በተለያዩ የትምህርት ዘርፎች በመጀመሪያና ሁለተኛ ድግሪ ያስተማራቸውን 1 ሺህ 79 ተማሪዎችን ነው ያስመረቀው፡፡

የወላይታ ዩኒቨርስቲ ፕሬዚዳንት ፕሮፌሰር ታከለ ታደሰ ኮቪድ-19 የመማር ማስተማር ስራዎች እንዲቋረጡ ያደረገ ቢሆንም በዛሬው ዕለት የተመረቁ ተማሪዎችን በቴክኖሎጂ በመታገዝ ትምህርታቸውን እንዲከታተሉ በማድረግ ማስመረቅ እንደተቻለ ገልፀዋል።

በመደበኛና በተከታታይ የትምህርት መርሃ ግብር ሰልጥነው ከተመረቁ ተማሪዎች መካከል 143ቱ ሴቶች ሲሆኑ፤ 47 ተማሪዎች ደግሞ በህክምና ዶክተሬት ሲመረቁ፤ ከእነዚህም 3ቱ ስፔሻላይዝድ ያደረጉ መሆናቸው ነው የተነገረው፡፡

የ2013 የትምህርት ዘመንን የኮሮና ቫይስን እየተከለካከሉ ለመጀመር አስፈላጊው ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን ፕሬዚዳንቱ ገልጸዋል፡፡

የሚዛን ቴፒ ዩኒቨርስቲም ትምህርታቸውን በበይነ መረብ በመታገዝ ተከታትለው ያጠናቀቁ 659 የመጀመሪያና ሁለተኛ ዲግሪ ተማሪዎችን አስመርቋል።

ከዚህ ውስጥ 63 በሁለተኛ ዲግሪ ትምህርታቸውን የተከታተሉ መሆናቸውን የዩኒቨርሲቲው ተጠባባቂ ፕሬዚዳንት ዶክተር አህመድ ሙስጠፋ ገልፀዋል፡፡

በቪዲዮ ኮንፈረስን መልዕክት ያስተላለፉት የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስትር ዲኤታ ዶክተር ሳሙኤል ክፍሌ በበኩላቸው ኢትዮጵያ ካለችበት ድህነት ተላቃ ወደ ሚገባት ብልፅግና ከፍታ እንድትደርስ የተመራቂዎች ሚና ከፍተኛ ነው ብለዋል፡፡

በጥላሁን ሁሴንና ተስፋዬ ምሬሳ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.