Fana: At a Speed of Life!

የደም እንባ የምታነባው ታዳጊ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 14፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ታዳጊዋ ከሰሞኑ የደም እንባ በማንባት በሃገረ ብራዚል አነጋጋሪ ሆናለች።

የ15 ዓመቷ ታዳጊ ብራዚላዊት ለአንድ ሳምንት ያክል  በእንባ ምትክ ደም ከአይኗ ሲወርድ ታይቷል ነው የተባለው።

እቺ ታዳጊ ከ12 ቀን በፊት ሆዷ ላይ ለተሰማት ህምም ወደ ሃኪም ቤት የሄደች ሲሆን፥ ሃኪሞችም የኩላሊት ጠጠር ምርመራ አድርገውላት ወደ ቤት ተመልሳ ነበር።

ሆኖም ብዙም ቀን ሳትቆይ ከአንድ ዓይኗ በሚወጣ ደም ምክንያት እንደገና ወደ ድንገተኛ ክፍል ተወስዳለች።

በዚህም ህክምና የተደረገላት ቢሆኑም የህክምና ባለሙዎች መፍትሔ ሊያመጡ አልቻሉም ነው ተባለው።

ይህ ሁኔታ አግራሞት የፈጠረባቸው የጤና ባለሙያዎችም “ይህ ለምን እንደሆኑ አናውቅም፤ ግራ ተጋብተናል” ብለዋል።

የታዳጊዋ እናት እንደምትናገረውም ልጄ ብዙ ምርመራ አድርጋለች ግን እስካሁን ሃኪሞች ምንም ችግር አላገኙም ብለዋል።

ከሆስፒታሉ ከተመለሱ ከሰዓታት በኋላም ደም ከሁለቱም ዓይኖቿ መፍሰስ ጀመረ ያሉ ሲሆን ይህም ቤተሰቡን የበለጠ አሳስቧል ነው ያሉት።

እንደገና ወደ ሆስፒታል ተወሰደች ግን ስለሁኔታዋ ማንም መልስ የሰጠ የለም ማለታቸው ተገልጿል።

ታዳጊዋ እንባ በሚፈስበት ወቅትም ምንም አይነት የህመም ስሜት እንደማይሰማት ትናገራለች።

ከመስከረም 13 ጀምሮ የደም እንባ በማንባት ላይ የምትገኘው ብራዚላዊት የደም እንባው በቀን ውስጥ በማንኛውም ጊዜ ሊታይ እንደሚችል ትናገራለች።

ምርመራ ያደረገላት ሆስፒታልም ያልተለመደው እንባ ምን እንደሆነ ለማወቅ ተጨማሪ ምርመራ ማድረግ አለብን ብሏል።

አንድ የአይን ሃኪም ግን አንዳንድ ጊዜ ህክምና ሳይደረግበት እና ያለ ምርመራ ውጤት በድንገት እንደታየው ይጠፋል ሲሉ የተናገሩ ሲሆን፥ በአንቲባዮቲክስ እና በሆርሞን መድኃኒቶች ሊታከም ይችላል ብለዋል።

ነገር ግን ይህ ሁኔታ አልፎ አልፎ ሌሎች የጤና ችግሮች እንደሚያስከትል ተናግረዋል።

ምንጭ፦ ኦዲቲ ሴንተራል

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.