Fana: At a Speed of Life!

የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች 11ኛ ክልል ሆኖ በይፋ ተመሰረተ

አዲስ አበባ ፣ ህዳር 14 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች 11ኛ ክልል ሆኖ በይፋ ተመሰረተ፡፡
 
የክልሉ ምስረታ ከአምስቱ ዞኖችና እና ከአንድ ልዩ ወረዳ የተወከሉ እንዲሁም ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በተገኙበት ነው በቦንጋ ከተማ የተካሄደው፡፡
 
የምዕራቦ ኦሞ ዞን፣ የቤንች ሸኮ ዞን፣ የካፋ ዞን፣ የዳውሮ ዞን እና የሸካ ዞን እንዲሁም የኮንታ ልዩ ወረዳ ህዝቦች በህዝበ ውሳኔ በአንድ ክልል ለመደራጀት መወሰናቸው ይታወሳል።
 
በቀጣይም የአዲሱ ክልል ረቂቅ ህገመንግስት ይፀድቃል፣ አፈጉባኤ ይመረጣል፣ ርዕሰ መስተዳድር ይሰየማል ተብሎ ይጠበቃል።
 
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.