Fana: At a Speed of Life!

ዲጂታል ኢትዮጵያን ዕውን ለማድረግ የባለድርሻ አካላት ቁርጠኝነት ወሳኝ ነው – ም/ጠ/ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 1፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) አፍሪካዊት የብልፅግናተምሳሌት የሆነች ሀገር የመገንባት ራዕይን ከግብ ለማድረስ ሁለንተናዊ የልማት ዕቅዶቻችን ሳይቆራረጡ መተግበር እንደሚገባ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ ገለጹ፡፡

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት ጽሑፍ ÷ ዛሬ በዓይነቱ የመጀመሪያ የሆነውን የፌዴራል ተቋማት የሱፐርቪዥን ሪፖርት ተከታትለናል ብለዋል፡፡

የልማት ዕቅዶችን ወደ ተግባር እንዲቀየሩ በተለያዩ ምዕራፎች በዕቅድ የሚሰሩ ሥራዎችን በተገቢው መንገድ መገምገም አስፈላጊ መሆኑን አጽንኦት ሰጥተዋል፡፡

በሱፐርቪዥኑ ሪፖርት በመልካም ጅማሮ የታየው ዋነኛው ጉዳይ ዲጅታላይዜሽን መሆኑን አስገንዝበዋል፡፡

የዲጂታል አገልግሎት ግልፅ፣ ተዓማኒነት ያለው፣ ፈጣን የአገልግሎት ስርዓት ደረጃ በደረጃ በመዘርጋት የህዝቡን ህይወት ለማሻሻል መሰረታዊ ተግባር ነው ሲሉም ገልጸዋል፡፡

ስለሆነም የዲጂታል ኢትዮጵያን ዕውን ለማድረግ የሁሉም ባለድርሻ አካላት ቁርጠኝነት ወሳኝ መሆኑን ነው የተናገሩት፡፡

በሱፐርቪዥኑ ሪፖርት የተገኙ መልካም ውጤቶችን ማጠናከር፣ ያሉ ችግሮችን እያረሙ እና እያስተካከሉ ተግባሩን ማስቀጠል እንደሚገባ አቅጣጫ ማስቀመጣቸውንም ጠቁመዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.