Fana: At a Speed of Life!

ኢትዮጵያና ቻይና ሐሰተኛ የጉዞ ሰነዶችን በሚለዩ ቴክኖሎጂዎች ላይ በጋራ ለመስራት ተስማሙ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 1፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ኮሚሽነር ጀነራል ደመላሽ ገ/ሚካኤል ከቻይና ብሔራዊ የኢሚግሪሽን አስተዳደር ም/ሃላፊ ኮሚሽነር ሊዩ ሃይታኦ ጋር ተወያይተዋል፡፡

በውይይታቸውም÷ ሁለቱ ተቋማት በቅንጅት እና በትብብር መስራት በሚችሉባቸው ጉዳዮች ዙሪያ መክረዋል፡፡

በተለይ ሕጋዊ የጉዞ ሰነዶችን ከሐሰተኛ ሰነዶች መለየት በሚያስችሉ ቴክኖሎጂዎች ዙሪያ ልምድ ለመለዋወጥ እና ድጋፍ ለማድረግ መስማማታቸው ነው የተገለጸው፡፡

ም/ኮሚሽነር ሊዩ ሃይታኦ÷ ኮሚሽነር ጀነራል ደመላሽ እንደ ዓለም አቀፍ የህዝብ ደህንነት ትብብር የዳይሬክተሮች ቦርድ አባልነታቸው በዓለም አቀፍ የህዝብ ደህንነት ዙሪያ ከፍተኛ ሚና እየተጫወቱ መሆኑን ተናግረዋል።

የቻይናው የሕዝብ ደኅንነት ሚኒስቴር መስሪያቤት ከኢትዮጵያ ፌደራል ፓሊስ ጋር የደረሰውን ስምምነት ለመተግበር ቁርጠኛ መሆናቸውን ገልጸዋል፡፡

ኢትዮጵያ በአፍሪካ ልዩ ሚና የምትጫወት ሀገር እንደሆነች ማንሳታቸውንም የፌዴራል ፖሊስ መረጃ ያመላክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.