Fana: At a Speed of Life!

የ2012 ሀገር አቀፍ ምርጫ የድምፅ መስጫ ቀን ነሐሴ 23 ሆኗል

አዲስ አበባ፣ የካቲት 6፣ 2012 ኤፍ.ቢ.ሲ) የ2012 ሀገር አቀፍ ምርጫ ተከልሶ በቀረበው የጊዜ ሰሌዳ መሰረት የድምፅ መስጫ ቀን ነሐሴ 23 ቀን 2012 ዓ.ም ሆኗል።

የምርጫ ባለድርሻ አካላት ኮንፈረንስ እየተካሄደ ነው።

በባለ ድርሻ አካላት ኮንፈረንሱ ላይ የምርጫ ሰሌዳ ማሻሻያውን የቦርዱ ሰብሳቢ ወይዘሪት ብርቱካን ሚደቅሳ አቅርበውታል ።

ከዚህ ቀደም ጊዜያዊ የድምፅ መስጫ ቀን ነሐሴ 10 ቀን እንዲሆን መወሰኑ ይታወሳል ።

የምርጫ ጊዜውን ለማራዘም የሚቀርቡ ጥያቄዎችን ግንዛቤ ውስጥ ብናስገባም ከህግ አንፃር የድምፅ መስጫ የተከለሰው ቀን ነሐሴ 23 ቀን 2012 ዓ.ም ይሆናል ብለዋል።

በክረምት መካሄዱ ሊፈጥር የሚችለውን ተፅእኖ በተመለከተም ከብሄራዊ ሜቲዮሮሎጂ ኤጀንሲ ጋር እየተሰራ መሆኑንም ተናግረዋል።

ከዝናቡ ስጋት አንፃር ወደ ነሐሴ ወር መውጫ ቀናት ድምፅ የመስጫ ቀኑ እንዲገፋ መደረጉን አንስተዋል።

በሃይለእየሱስ መኮንን

ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የቴሌግራም ገፃችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ!
https://t.me/fanatelevision

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.