Fana: At a Speed of Life!

የ2021 የሕክምና ዘርፍ የኖቤል ሽልማት 2 ተመራማሪዎች በጋራ አሸነፉ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 25፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የ2021 የፊዚዮሎጂ ወይም የሕክምና ዘርፍ የኖቤል ሽልማት ዴቪድ ጁሊየስ እና አርደም ፓታፑቲያን የተባሉ ተመራማሪዎች በጋራ እንዳሸነፉ ተሰማ፡፡

ውሳኔው የተላለፈው በትናንትናው እለት በስዊድን ካሮሊንስካ ኢንስቲትዩት በተሰየመው ጉባዔ መሆኑ ተገልጿል።

ተመራማሪዎቹ ሽልማቱን ያሸነፉት÷ ለሙቀት እና በእንቅስቃሴ ወቅት የሚሰማንን ስሜት በመለየት ምላሽ የሚሰጡትን ነርቭ እና የስሜት ሕዋሳት በማመላከታቸው እንደሆነ ነው የተመላከተው፡፡

ዴቪስ ጁሊየስ የተባለው አሜሪካዊ ፊዚዮሎጂስት ሳንፍራንሲስኮ በሚገኘው ካሊፎርኒያ ዩኒቨርሲቲ ውስጥ በመስራት ላይ የሚገኝ ተመራማሪ ሲሆን÷ ለሽልማት ያበቃው ግኝትም፣ በቆዳ ነርቭ ላይ የሚገኝ ለሙቀት በፍጥነት ምላሽ የሚሰጠውን ሕዋስ ለይቶ ማመላከቱ ነው፡፡

አርመን አሜሪካዊው ሞለኪውላር ባዮሎጂስት እና ኒውሮ ሳይንቲስቱ ፓታፑቲያን ደግሞ ለሽልማት የበቃው በእንቅስቃሴ ወቅት ለሚሰማን ስሜት ምላሽ የሚሰጡ በቆዳ እና በውስጥ የሰውነታችን ክፍል የሚገኙ ሕዋሳትን በጥናቱ በመለየቱ እንደሆነ ነው የተገለፀው፡፡

ሁለቱም አዲስ ግኝቶች የነርቭ ስርዓታችን እንዴት ለሙቀት፣ ለቅዝቃዜ እና ለንክኪ ምላሽ እንደሚሰጡ ያመላከተና የተጠቀሱት ስሜቶችም በርካታ አካላዊ ሁኔታዎችንና የሕመም ስሜቶችን በማመላከትም ረገድ ጠቃሚ ናቸው ተብሏል፡፡

በዓለማየሁ ገረመው

ምንጭ ፡-ሲጂቲ ኤን

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.