Fana: At a Speed of Life!

ዳያስፖራው የተለያዩ መረጃዎች የሚያገኝበት ማዕከል ወደ ስራ ገባ

አዲስ አበባ ፣ ታህሳስ 20 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ዳያስፖራው የተለያዩ መረጃዎችን የሚያገኝበት አዲስ የዳያስፖራ ማዕከል ወደ ስራ ገባ።
 
ማዕከሉን ወደ ስራ የማስገባት ስነስርዓት የተካሄደ ሲሆን በስነስርዓቱ ላይ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤን ጨምሮ ከፍተኛ የመንግስት የስራ ሀላፊዎችና የዳያስፖራ ተወካዮች ተገኝተዋል።
 
ማዕከሉ የበዓል ቀናትን ጨምሮ ከእሁድ እስከ እሁድ አገልግሎት የሚሰጥ ሲሆን በኢኮኖሚው መስክ ያለውን አጠቃላይ እንቅስቃሴ የተመለከቱ መረጃዎችን ለዳያስፖራው ተደራሽ የሚያደርግ ነው።
 
ማህበራዊ ኑሮን የሚያሻሽሉ ስራዎችን በተመለከተ መረጃዎች የሚያገኙበት ስርዓት መዘርጋቱንም ለማወቅ ተችሏል።
 
በማዕከሉ የአንድ መስኮት አገልግሎት የሚሰጥ ሲሆን ወሳኝ ኩነትና ኢሚግሬሽን አገልግሎትም ዳያስፖራው የሚያገኝ ይሆናል።
 
ዳያስፖራውን በተመለከተ ስለተዘጋጁ ልዩ ልዩ ሁነቶችም በማዕከሉ ገለፃ እንደሚደረግ ኢዜአ ዘግቧል።
 
 
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.