Fana: At a Speed of Life!

የዳያስፖራውን ማህብረሰብ ያሳተፈ የአረንጓዴ አሻራ የችግኝ ተከላ መርሀ ግብር ተካሄደ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 26፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) መርሀ ግብሩ በርካታ የዳያስፖራ አባላት በተገኙበት በአዲስ አበባ ከተማ በተዘጋጀው የዳያስፖራ ፓርክ ውስጥ ተካሂዷል፡፡
በችግኝ ተከላ መርሃግብሩ መልዕክት ያስተላለፉት ከንቲባ አዳነች አቤቤ ፥ትውልድ እንዲማርና ወቅቱን እንዲያስብ በማለም የተካሄደ መሆኑን ተናግረዋል፡፡
ለዳያስፖራው መታሠቢያ ይሆን ዘንድና አካባቢን ለማልማት ከተማ አስተዳደሩ የዳያስፖራ ፓርክ ማዘጋጀቱን ተናግረዋል።
መታሠቢያ ትርጉሙ ከአረንጓዴ ልማት በላይ ነው ያሉት ከንቲባ አዳነች አቤቤ፥ የዳያስፖራው የአረንጓዴ አሻራ ተሳትፎም እንደሚያበረታታ ገልጸዋል።
በመርሀ ግብሩ የተሳተፉ ዳያስፖራዎች የእናት አገር ጥሪን ተቀብለው አሻራ ለማኖር መብቃታቸው ልዩ ስሜት እንደፈጠረባቸው ገልጸዋል።
በቀጣይም መሰል ተሳትፎዎችን በማጉላት አገርን በሁሉም መስክ ለመደገፍ ዝግጁ መሆናቸውን ከከተማ አስተዳደሩ ፕሬስ ሰክሬተሪያት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.