Fana: At a Speed of Life!

ጃፓናዊ የማልቀስ አስተማሪ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 5፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ጃፓናዊው የማልቀስ አስተማሪ ማልቀስ ጭንቀትን ለማቃለል ጠቀሜታ እንዳለው ይገልጻል።

ሂድፉሚ ዮሺዳ ራሱን “የማልቀስ አስተማሪ” ሲል ይገልጻል፤ ጭንቀትን ለማቃላል እንዲሁም ደስተኛ ሕይወት ለመምራት ማልቀስ እንደሚገባ ይናገራል።

ሂድፉሚ ዮሺዳ ያለፉትን ስምንት ዓመታት ሰዎች ማልቀስን ማለማመድ እና ማስተማር መቻሉንም ይናገራል።

ጃፓናውያን መጀመሪያ ላይ በቀላሉ ለማልቀስ ዝንባሌ ነበራቸው ያለው መረጃው ሆኖም ይህ የማልቀስ ልምዳቸው በልጆች ሆነ በአዋቂዎች እየቀረ መምጣቱ ተነስቷል።

ግለሰቡ ይህን መሰል ልምድን በመቀየር በማልቀስ ጭንቀትን ማስወገድ እንዲሁም ዘና ማለት ማልቀስ ከሚያመጣልን ጥቅሞች አንዱ ነው ይላል።

በዚህም ላለፉት ሰባት ዓመት ተኩል ከ50 ሺህ በላይ ሰዎች እንዲያነቡ ድጋፍ አድርጓል ነው የተባለው።

የ45 ዓመቱ የማልቀስ አስተማሪው በመደበኛነት ወርክሾፖችን እና ንግግሮችን በመላው ጃፓን በማዘጋጀት በሳምንት አንድ ጊዜ ማልቀስ የሚያስገኘውን ጥቅም በማስተማር እና እንዲያለቅሱ በማበረታታት ደስተኛ እና ከጭንቀት እንዲርቁ በማገዝ ላይ ይገኛል ነው የተባለው።

ማልቀስ የልብ ምት ፍጥነትን የሚቀንስ፣ አእምሮን የሚያረጋጋ እንዲሁም የነርቭ እንቅስቃሴን በማነቃቃት ለአእምሮ ጤንነት ትልቅ ጥቅም ያስገኛል ሲልም ይገልጻል።

ምንጭ፡- ኦዲቲ ሴንትራል

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.