Fana: At a Speed of Life!

ጠ/ሚ ዐቢይ በቤኒሻንጉል ጉሙዝ መተከል ዞን ነዋሪዎች ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ ፣ ታህሳስ 13 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ከመተከል ዞን ነዋሪዎች ጋር ተወያዩ።

በውይይት መድረኩ ላይ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ አሻድሊ ሀሰን፣ የሰላም ሚኒስትር ሙፈሪያት ካሚል፣ የኢፌዴሪ መከላከያ ሰራዊት ጠቅላይ ኤታማጆር ሹም ጄኔራል ብርሃኑ ጁላ እና ሌሎች የስራ ሀላፊዎች ተገኝተዋል።

ውይይቱ በመተከል ዞን በተደጋጋሚ የሚከሰቱ የፀጥታ ችግሮችን ለማስቆም ዘለቄታዊ የመፍትሔ  አቅጣጫ  ለማስቀመጥ ያለመ  ነው።

በወቅቱም ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ  አሕመድ ለሀገሪቱ አንድነትና ሠላም ብቸኛው አማራጭ ኢትዮጵያውያን  ከጥላቻ፣ ከስሜት እና ከመገፋፋት ወጥተው አንድነታቸውን እና አብሮነትን ማጠናከር ነው ብለዋል።

በቀጠናው የተፈጠረውን የፀጥታ ችግር በዘላቂነት ለማስቆም ጥረት የተደረገ ቢሆንም በርካታ ተዋናዮች በመኖራቸው ችግሩን በአፋጣኝ እንዳይቆም አድርጎት ቆይቷልም ነው ያሉት።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ አያይዘውም አካባቢውን ወደ ሠላም የመመለሱ ሥራ በትኩረት እንደሚሠራ ገልጸዋል፡፡

ከዚህ ባለፈም በዞኑ እየተካሄደ ያለው የህግ ማስከበር ተግባር ገለልተኛ እና ከአድሏዊነት በፀዳ መልኩ እንዲተገበርም ጠቅላይ ሚኒስትሩ  አሳስበዋል።

በስሜት እና በብሶት የጁንታውን የጥፋት ተልዕኮ ተቀብሎ ወደ ጫካ የሸሸው ኃይል በሠላማዊ መንገድ እንዲመለሱ ለማድረግ አመራሩና በየደረጃው ያሉ ባለድርሻ አካላት ኃላፊነታቸውን እንዲወጡም ጠቅላይ ሚኒስትሩ ጥሪ አቅርበዋል።

በተጨማሪም የክልሉን የተፈጥሮ ፀጋ በመጠቀም ሥራ አጥ ወጣቶችን  በማደራጀት የክልሉ መንግሥት ተጠቃሚ ለማድረግ በትኩረት እንዲሰራም መልዕክተ አስተላልፈዋል፡፡

መንግሥት እየወሰደው ካለው እርምጃ ባሻገር በቀጠናው ዘላቂ ሠላም እንዲሰፍን ሀገር ሽማግሌዎች፣ የሃይማኖት አባቶች፣ የወጣቶችና የሴቶች አደረጃጀቶች ጋር በዞኑ የተፈጠረውን የሠላም እጦት ለመፍታት  ያለሰለሰ ጥረት እንዲያደርጉም ጥሪ አቅርበዋል።

የውይይቱ ተሳታፊዎችም ኃላፊነት የጎደለው የማህበራዊ ሚዲያ አጠቃቀም እና ባለፋት 27 አመታት ህወሓት የፈፀመው የፖሊቲካ አሻጥር በቀጠናው ዘላቂ ሠላም እንዳይረጋገጥ  አድርጎ መቆየቱን ተናግረዋል።

በመተከል ዞን ተደጋጋሚ የሚፈጠረውን የጸጥታ ችግር ለማስቆም ጥረት ቢደረግም አባባሽ ምክንያቶችን ለይቶ መፍትሄ መፍትሄ መስጠት ባለመቻሉ የፀጥታ ችግሩ እስካሁን መቀጠሉን  አንስተዋል።

ተሳታፊዎቹ  አያይዘውም ዞኑ የተለያዩ ብሔር፣ ብሄረሰቦችና ህዝቦች ለዘመናት በአብሮነት የሚኖሩበት አካባቢ  እንደመሆኑ መጠን የህዝቦችን አንድነትና አብሮነትን ለማጠናከር መንግሥት በትኩረት ሊሠራ ይገባልም ብለዋል።

በብዙአለም ቤኛ

 

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤

ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ

ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ

ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.