Fana: At a Speed of Life!

ፕሬዚዳንት ሳልቫ ኪር ለሰላሳ የህግ ታራሚወች ይቅርታ አደረጉ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 25፣ 2012 (ኤፍቢሲ) የደቡብ ሱዳን ፕሬዚዳንት ሳልቫ ኪር ለሠላሳ የህግ ታራሚወች ይቅርታ አደረጉ።

በፕሬዚዳንቱ ውሳኔ ለሰላሳ የህግ ታራሚወች ይቅርታ መደረጉን የሃገሪቱ መገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል።

ምህረት ከተደረገላቸው መካከል የፖለቲካ ተሟጋቹ ፒተር ቢያር እና ካርቢና ወል የተባለ ነጋዴ ይገኙበታል ተብሏል።

ይቅርታው ፕሬዚዳንቱ በአዲስ አመት ዋዜማ በጁባ ማዕከላዊ እስር ቤት ጉብኝት ካደረጉ በኋላ የተደረገ ነው።

በዚህም በማረሚያ ቤቱ መልካም ስነ ምግባር ያሳዩና ቀላል ወንጀል የፈጸሙ ታራሚወች ይቅርታ ተደርጎላቸዋል ነው የተባለው።

የፕሬዚዳንቱ ይቅርታ የደቡብ ሱዳን ተቀናቃኝ ሃይሎች ለደረሱት የሰላም ስምምነት ተግባራዊነት ማሳያ ተደርጎ ተወስዷል።

የፖለቲካ ተሟጋቹ ፒተር ቢያር የሃገሪቱን ደህንነት አደጋ ላይ ለመጣል ሞክሯል በሚል ባለፈው የፈረንጆች አመት ሰኔ ወር ላይ በቁጥጥር ስር መዋሉ ይታወሳል።

ቢያር በሐምሌ ወር 2018 በብሔራዊ ደህንነት አገልግሎት በቁጥጥር ስር ውሎ ሁለት ዓመት ተፈርዶበት ነበር።

ግለሰቡ አመፅ በማነሳሳት እና ሰላምን በማደፍረስ ሲከሰስ ካርቢና ወል ደግሞ በማጭበርበር ወንጀል ተጠርጥሮ በቁጥጥር ስር መዋሉን መረጃዎች ያመላክታሉ።

ምንጭ፦ ሲ ጂ ቲ ኤን

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.