Fana: At a Speed of Life!

ፕሬዚዳንት ፑቲን ሩሲያ የሚጣልባትን የኢኮኖሚ ማዕቀብ የመቋቋም አቅም እንዳላት ተናገሩ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 11፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ፕሬዚዳንት ቪላድሚር ፑቲን ምዕራባውያን አገራቸውን በኢኮኖሚ ማዕቀብ ጫና ውስጥ ለመጣል የሚያደርጉትን ጥረት ሀገራቸው እንደምትቋቋመው ተናገሩ።

ፕሬዚዳንቱ ትናንት በቅዱስ ፒተርስበርግ በተካሄደው የኢኮኖሚ ጉባኤ ላይ “እኛ ጠንካሮች ነን እና ማንኛውንም ፈተና መቋቋም እንችላለን፤ ማንኛውንም ችግር እንፈታዋለን፤ የአገራችን የሺህ አመት ታሪክ ስለዚህ ጉዳይ ይናገራል” ነው ያሉት።

በየካቲት ወር መጨረሻ ላይ ወደ ዩክሬን ልዩ ወታደራዊ ዘመቻ እንዲካሄድ ከማዘዛቸው በፊት ፑቲን ዩክሬን ወደ ሰሜን አትላንቲክ ጦር ቃል ኪዳን ድርጅት /ኔቶ/ እንደማትገባ ከአሜሪካ ዋስትና ጠይቀው እንደነበር አስታውሰዋል።

“በእኛ ላይ ዛቻዎች እየጨመሩ ከሚሄዳቸው የተነሳ ሩሲያ ልዩ ወታደራዊ ዘመቻ ለማካሄድ ተገዳለች ያሉት ፑቲን ውሳኔው ግን ከባድ እንደነበር ተናግረዋል፡፡

በትናንቱ መድረክ ላይ የሀገሪቱን “ግዙፍ አቅም” እውን ለማድረግ እና ምዕራባውያን የሩሲያን ኢኮኖሚ ለማዳከም የሚያደርጉትን ጥረት ለማክሸፍ የሩሲያ ኩባንያዎች የሀገር ውስጥ ኢንቨስትመንታቸውን እንዲያሳድጉ ማሳሰባቸውን ሲ ጂ ቲ ኤን ዘግቧል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.