Fana: At a Speed of Life!

ህጻናትን የመረዘችው ቻይናዊቷ መምህር የሞት ፍርድ ተፈረደባት

አዲስ አበባ፣ መስከረም19 ፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ቻይናዊቷ የህጻናት መምህር 25 ልጆችን በመመረዝ እና አንድ ህጻንን ለህልፈት በመዳረጓ ምክንያት የሞት ፍርድ ተፈርዶባታል።
ባለፈው ዓመት ጂያዝኦ ከተማ ውስጥ በሚገኝ አንድ መዋዕለ ህፃናት ውስጥ ያሉ ሕፃናት የጠዋት ቁርሳቸውን ገንፎ ከተመገቡ በኋላ ወደ ሆስፒታል መወሰዳቸውን ተከትሎ ዋንግ ዩን በቁጥጥር ስር መዋሏ ተነግሯል፡፡
መምህርቷ ከተማሪ አስተዳደር ጉዳዮች ጋር በተገናኘ ከስራ ባልደረቦቿ ጋር መጨቃጨቋንና ለበቀል በመነሳሳት የስራ ባልደረቦቿ በሚያስተምሯቸው ተማሪዎች ምግብ ላይ ሶዲየም ናይትሬትን መጨመሯን ፍርድ ቤቱ ገልጻል፡፡
በዚህም ፍርድ ቤቱ ድርጊቱን ጭካኔ የተሞላበት ርካሽ ተግባር ሲል ገልጾታል።
ፍርድ ቤቱ አክሎም ወይዘሮ ዋንግ ሰዎችን በመመረዝ ይህ የመጀመሪያዋ አለመሆኑን በመግለጽ ቀደም ሲል ኒትሬት በተባለ ንጥረ ነገር የገዛ ባለቤቷን መመረዟን ጠቅሷል፡፡
ይህንን ተከትሎም በትናንትናው ዕለት በጂያዝኦ ውስጥ የሚገኝ አንድ የአከባቢው ፍርድ ቤት መምህርት ዋንግ ላይ የሞት ፍርድ መፍረዱን ግሎባል ታይምስ ጋዜጣ ዘግቧል፡፡
ባለፈው ዓመት መጋቢት ወር ላይ የመምህርቷ ድርጊት ሲሰማ መላው ቻይናውያንን ያስደነገጠና ዓለም አቀፍ ዓብይ ዜና ሆኖ ነበር።
በወቅቱ 23ቱም ተማሪዎች ቁርሳቸውን ከተመገቡ በኋላ ማስመለሳቸውንና ራሳቸውን መሳታቸውም ይታወሳል።
ሶድየም ናይትሬት አብዛኛውን ጊዜ ስጋን ለማከም እንደ ምግብ ያገለግላል ሆኖም መጠኑ ከፍተኛ ሲሆን መርዛማ ሊሆን ይችላል ተብሏል፡፡
ምንጭ፡-ቢቢሲ
የዜና ሰዓት ሳይጠብቁ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ትኩስ እና ሰበር ዜናዎችን በፍጥነት በአጭር የፅሁፍ መልዕክት መልክ በስልክዎ ላይ እንዲደርስዎ ወደ 8111 OK ብለው ይላኩ።
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.