Fana: At a Speed of Life!

ለረጅም ወራት የቪዲዮ ጌም የተጫወተው ታዳጊ ለጭንቅላት ውስጥ ደም መፍሰስ ተጋልጧል

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 10፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የ15ዓመቱ ታዳጊ ያለማቋረጥ ለረጅም ወራት የቪዲዮ ጌም ከተጫወተ በኋላ ለጭንቅላት ውስጥ ደም መፍሰስ (ስትሮክ) ተጋላጭ መሆኑ ተሰማ፡፡

ቻይናዊው የ15 ዓመት ታዳጊ ከአምስት ወራት በላይ የቪዲዮ ጌም ከተጫወተ በኋለ ለጭንቅላት ውስጥ ደም መፍሰስ ተጋላጭ የሆነ ሲሆን ግራ እጁም የማይታዘዝ ሆኗል ነው የተባለው፡፡

ታዳጊው ለረጅም ሰዓት ከመጫወቱም ባሻገር ለሁለት ሰዓታት ብቻ እንቅልፍ እንደሚያገኝ ታውቋል፡፡

እንደ ቤተሰቦቹ ገለፃም ቻይናዊው ታዳጊ በኮሮና ቫይረስ ሳቢያ ትምህርት ቤቶች መዘጋታቸውን ተከትሎ የራሱ ክፍል ውስጥ በበቀጥታ (ኦንላይን) ትምህርቱን እንዲከታተል ቢነገረውም አብዛኛውን ጊዜውን እና ሌሊቱን የቪዲዮ ጨዋታዎች በመጫወት አሳልፏል፡፡

በዚህ ሳቢያም ታዳጊው እጁ መታዘዝ ማቆሙን የህክምና ባለሙያዎች ገልጸዋል፡፡

እንዲሁም በነበረው የምግብ እና የእረፍት እጥረት በአንጎሉ ውስጥ የደም እና የኦክስጂን መጠን እንዲቀንስ ከማድረጉም በላይ ለጭንቅላት ውስጥ ደም መፍሰስ እንዲዳረግም ምክንያት ሆኗል ተብሏል።

ታዳጊው የህክምና እርዳታ እየተደረገለት የሚገኝ ቢሆንም ሙሉ በሙሉ ማገገም ወይም የግራ እጁን ጤንነት ወደ ቀድሞው መመለስ ከባድ መሆኑንም የህክምና ባለሙያዎቹ ተናግረዋል፡፡

እንዲሁም መሰል አጋጣሚዎች በታዳጊዎች ላይ ያልተለመዱ መሆናቸውን የህክምና ባለ ሙያዎቹ አንስተዋል፡፡

ምንጭ፡- ኦዲቲ ሴንትራል

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.