Fana: At a Speed of Life!

መንግሥት በውስጥ ጉዳዩ ሕግና ሥርዓትን የማስከበር ሙሉ አቅም አለው -አምባሳደር ነብያት ጌታቸው

አዲስ አበባ ፣ህዳር 23 ፣2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በአልጀሪያ የኢፌዴሪ ኤምባሲ ባለሙሉ ሥልጣን አምባሳደር ነብያት ጌታቸው ከሬዲዮ አልጄሪያ ዓለም አቀፍ አገልግሎት ጋር በነበራቸው ቆይታ የፌደራል መንግስት በትግራይ ክልል እየሰራ ያለው ህግ የማስከበር ስራ በህግ የተሰጠውና በህገ-መንግስት በተደነገገው መሠረት ሊስተናገድ የሚችል የውስጥ ጉዳይ ነው ሲሉ ገልጸዋል ፡፡
በመሆኑም መንግሥት በውስጥ ጉዳዩ ሕግንና ሥርዓትን የማስከበር ሙሉ አቅም አለው ብለዋል፡፡
በትግራይ ክልል የተካሄደው የህግ ማስከበር ዘመቻ በአጭር ጊዜ በድል መጠናቀቁና ቀጣዩ ሥራ ተፈላጊ የሆኑትን የአጥፊውን የጁንታውን አባላት በቁጥጥር ሥር አውሎ ለህግ የማቅረብ ጉዳይ መሆኑን ገልፀዋል፡፡
አምባሳደሩ አያይዘውም አጥፊው ቡድን ጉዳዩን ክልላዊና ዓለም ዓቀፋዊ ይዘት እንዲኖረው ያደረገው ሙከራም መክሸፉን አብራርተዋል፡፡
የአፍሪካ ኀብረትን ጨምሮ በዓለም ዓቀፍ ድርጅቶች በኩል የቀረቡ የውይይት ጥሪዎች ቢኖሩም መንግሥት በውስጥ ጉዳዩ ሕግንና ሥርዓትን የማስከበር ሙሉ አቅም ያለው መሆኑንና በዚህ ወቅት ከወንጀለኞች ጋር መደራደር ሳይሆን ለሕግ የማቅረብ ሕገ-መንግሥታዊ ኃላፊነቱን እንደሚወጣ ገልፀዋል፡፡
በክልሉ በቀጣይ በሚከናወኑ የመልሶ ማቋቋምና የሰብዓዊ ዕርዳታ ጉዳዮች ዙሪያ በክልሉ ከተቋቋመው ጊዜያዊ አስተዳደር ጋር ውይይቶች እየተደረጉ እንደሆኑ መግለጻቸውን በአልጀሪያ ከሚገኘኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።
ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል www.youtube.com/fanatelevision ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.