Fana: At a Speed of Life!

ሴኔጋል እና ሞሮኮ በካሜሮን የአፍሪካ ዋንጫ ሩብ ፍጻሜውን ተቀላቀሉ

አዲስ አበባ፣ጥር 18፣2014 (ኤፍ ቢሲ) ሴኔጋል እና ሞሮኮ በካሜሮን የአፍሪካ ዋንጫ ተጋጣሚወቻቸውን በማሸነፍ ሩብ ፍፃሜውን ተቀላቅለዋል፡፡

ምሽት አንድ ሰዓት በተደረገው ጨዋታ ሴኔጋል ኬፕ ቬርዴን 2 ለ 0 በማሸነፍ ነው ሩብ ፍፃሜውን መቀላቀል የቻለችው፡፡

ሴኔጋል ብልጫ በወሰደችበት ይህ ጨዋታ የማሸነፊያ ጎሎችን ሳዲዮ ማኔ እና ባምባ ዲዬንግ ከእረፍት መልስ አስቆጥረዋል፡፡

ኬፕ ቬርዴ በጨዋታው ሁለት ተጫዋቾችን በቀይ ካርድ ያጣች ሲሆን፥ በዚህም በካሜሩን የአፍሪካ ዋንጫ በአንድ ጨዋታ ሁለት ተጫዋቾችን በቀይ ካርድ ያጣች የመጀመሪያዋ ሀገር ሆናለች፡፡

ሁለቱ ቡድኖች ትናንት ምሽት በደጋፊዎች እና በፀጥታ አካላት በተፈጠረው የኦሌምቤ ስታዲየም ግጭት ህይወታቸውን ያጡ ወገኖችን በማሰብ ጨዋታቸውን አከናውነዋል፡፡

በተመሳሳይ ምሽት 4 ሰዓት ላይ በተደረገ ጨዋታ ሞሮኮ ማላዊን በማሸነፍ ሩብ ፍፃሜውን መቀላቀል ችላለች፡፡

የሞሮኮን የማሸነፊያ ጎሎች አሽራፍ ሀኪሚ እና የሱፍ ነሲሪ ሲያስቆጥሩ የማላዊን ብቸኛ ጎል ጋባዲኖ መሃንጎ አስቆጥሯል፡፡

የአፍሪካ ዋንጫ መርሃ ግብሮች ዛሬም ሲቀጥሉ ምሽት አንድ ሰዓት ላይ አይቮሪኮስት ከግብፅ የሚያደርጉት ጫዋታ ተጠባቂ ሲሆን ምሽት 4 ሰዓት ደግሞ ማሊ አኳቶሪያል ጊኒን ትገጥማለች፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.