Fana: At a Speed of Life!

ቅዱስጊዮርጊስ የፕሪሚየር ሊጉ አሸናፊ ሲሆን አዲስ አበባ ከተማ ሶስተኛው ወራጅ ሆኗል

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 24 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ቅዱስ ጊዮርጊስ የ2014 የቤት ኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ አሸናፊ መሆኑን አረጋገጠ።

በ30ኛ ሳምንት የሊጉ መርሐ ግብር ቅዱስ ጊዮርጊስ ከአዲስ አበባ ከተማ ጋር ጨዋታውን አድርጎ ድል ቀንቶታል።

ጨዋታውን ቅዱስ ጊዮርጊስ 4 ለ 0 ሲያሸንፍ ኢስማኤል አሮ ኦጎሮ እና አማኑኤል ገብረሚካኤል የድል ጎሎቹን አስቆጥረዋል።

ውጤቱን ተከትሎም ፈረሰኞቹ የ2014 የቤት ኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ አሸናፊ መሆኑን አረጋግጧል።

ለዋንጫው እስከ መጨረሻው ሳምንት ድረስ ተፎካካሪ ሆነው የዘለቁትና ዋንጫውን ለማንሳት ከማሸነፍ ባለፈ የፈረሰኞቹን ነጥብ መጣል ሲጠብቁ የነበሩት ፋሲል ከነማዎች ውድድሩን በሁለተኝነት አጠናቀዋል።

በሊጉ የመጨረሻ ዙር በርካታ ነጥቦችን በመሰብሰብ እስከ መጨረሻው የዋንጫ ተፋላሚ የሆነው ፋሲል ከነማ ከድሬዳዋ ከተማ ጋር ባደረገው ጨዋታ 3 ለ 2 ለ ተሸንፏል።

በረከት ደስታ እና በዛብህ መለዩ ለአጼዎቹ ጎሎቹን ሲያስቆጥሩ ጋዲሳ መብራቴ፣ ሄኖክ አየለ እና አብዱራህማን ሙባረክ የድሬዳዋ ከተማን የድል ጎሎች አስቆጥረዋል።

ውጤቱን ተከትሎም ድሬዳዋ ከተማ ነጥቡን 33 በማድረስ በፕሪሚየር ሊጉ መቆየቱን አረጋግጧል።

በአንጻሩ በቅዱስ ጊዮርጊስ የተሸነፈው አዲስ አበባ ከተማ ሰበታ ከተማ እና ጅማ አባ ጅፋርን ተከትሎ የወረደ ሶስተኛው ክለብ ሆኗል።

የመውረድ ስጋት ውስጥ የነበረው አዳማ ከተማ የመጨረሻ ጨዋታውን ሐዋሳ ከተማን 3 ለ 2 በማሸነፍ በፕሪሚየር ሊጉ መቆየቱን አረጋግጧል።

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.