Fana: At a Speed of Life!

በሁለተኛው የዓለም ጦርነት በወንዝ ውስጥ ሰምጦ የነበረ ቦንብ ሳይፈነዳ ተገኘ

አዲስ አበባ ፣ ነሐሴ 2 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ጣሊያን ውስጥ በሁለተኛው የዓለም ጦርነት በወንዝ ውስጥ ሰምጦ እስከዛሬ ሳይፈነዳ የቆየ ግዙፍ ቦንብ በድርቅ ምክንያት መገኘቱ ተዘገበ።

450 ኪሎ ግራም ወይም 1ሺ ፓውንድ የሚመዝነው ይህ ቦምብ በድርቅ ምክንያት በተመናመነው ወንዝ ዳርቻ ላይ በአሳ አጥማጆች እንደተገኘ ነው የተገለፀው።

የአገሪቱ ወታደራዊ ባልሥልጣናት በሰጡት ማብራሪያ ፥ ያለፈነዳው ይህ ቦንብ 240 ኪሎ ግራም የሚመዝን ፈንጂ መያዙን ተናግረዋል።

ቦንቡ በጥንቃቄ እንዲፈነዳና እንዲበተን ለማድረግ ሲባልም ወደ 3 ሺ የሚጠጉ ነዋሪዎች ከአካባቢው እንዲነሱ መደረጉም ተገልጿል።

በጣሊያን ከ70 ዓመታት በኋላ በተከሰተው አስከፊ ድርቅ ያልተለመደ ሞቃታማ የአየር ሁኔታ እና ዝቅተኛ የዝናብ መጠን በመፈጠሩ በሰሜናዊ ጣሊያን ያለውን የውሃ እጥረት እና የአየር ንብረት ለውጥ ከፍ ያደረገው ሲሆን፥ የጣሊያኑ ትልቁ እና 650 ኪሎ ሜትር ይጓዝ የነበረው ፖ ወንዝ እየደረቀ መምጣቱም ተጠቁሟል።

የሀገሪቱ ወታደራዊ ባለስልጣን ኮሎኔል ማርኮ ናሲ ለሮይተርስ የዜና ወኪል እንደተናገሩት፥ በከፍተኛ ድርቅ ምክንያት በሁለተኛው የዓለም ጦርነት በጣሊያን ፖ ወንዝ ውስጥ ሰምጦ የቆየውና ያልፈነዳው ቦምብ በወንዙ ዳርቻ ላይ በዓሳ አጥማጆች አማካይነዝት የተገኘ መሆኑን ቢቢሲ ዘግቧል።

ቦምቡ በትናንትናው እለት በባለሙያዎች አማካይነት ጥንቃቄ በተሞላበት መንገድ እንዲፈነዳና እንዲበተን ለማድረግ ተችሏል።

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.