Fana: At a Speed of Life!

በሐረሪ ክልል የዋጋ ንረት እንዲባባስ ያደረጉ 38 የንግድ ድርጅቶች ታሸጉ

አዲስ አበባ ፣ ሐምሌ 29 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በሐረሪ ክልል ምርቶችን በመደበቅ የዋጋ ንረት እንዲባባስ ያደረጉ 38 የንግድ ደርጅቶች መታሸጋቸውን የክልሉ ንግድና ልማት ኤጀንሲ አስታወቀ።

የኤጀንሲው ኃላፊ አቶ ቡሽራ አልዪ እንደገለጹት÷ የታሸጉት የንግድ ድርጅቶች ምርቶችን በመደበቅ የዋጋ ንረት የፈጠሩ የምርት አከፋፋይና ነጋዴዎች ንብረቶች ናቸው።

በሸዋበርና አራተኛ ገበያዎች በተደረገ ክትትል እንዲታሸጉ የተደረጉት የንግድ ድርጅቶቹ የምግብ ፍጆታ ምርቶች ያለአግባብ በማከማቸታቸውና አላስፈላጊ የዋጋ ጭማሪ እንዲከሰት በማድረጋቸው ነው ማለታቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

በክልሉ አንዳንድ ነጋዴዎች እየፈጠሩት ያለውን የተጋነነ የዋጋ ንረት ለመቆጣጠር ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመቀናጀት ክትትልና ቁጥጥር እየተደረገ መሆኑንም ኃላፊው አመልክተዋል።

ህብረተሰቡም አጥፊዎችን በመጠቆም ንቁ ተሳትፎ በማድረግ ላይ እንደሚገኝ አስታውቀዋል።

በቀጣይም ከህዝቡና ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመቀናጀት የዋጋ ንረት የሚያባብሱ ነጋዴዎችን በመለየት ስርዓት የማሲያዙ ስራ እንደሚቀጥል አቶ ቡሽራ ገልጸዋል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.