Fana: At a Speed of Life!

በብራዚል በኮሮና ቫይረስ ህይወታቸው ያለፈ ሰዎች ቁጥር ከ100 ሺህ አለፈ

አዲስ አበባ ፣ ነሀሴ 3 ፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በብራዚል በኮሮና ቫይረስ ሕይወታቸው ያለፈ ሰዎች ቁጥር ከ100 ሺህ ማለፉ ተገለጸ።

በሀገሪቱ በሦስት ወር ጊዜ ውስጥ በበሽታው 50 ሺህ ሰዎች ህይወታቸው ያለፈ ሲሆን÷ በ50 ቀናት ውስጥ ብቻ እጥፍ መጨመሩን መረጃዎች ያመላክታሉ።

በዚህም በብራዚል በኮሮና ቫይረስ ህይወታቸው ያለፈ ሰዎች ቁጥር የ100 ሺህ 477 የደረሰ ሲሆን ÷በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር ደግሞ ከ 3 ሚሊየን ማለፉ ተነግሯል።

ይህም ሀገሪቱ በዓለም ወረርሽኙ ክፉኛ ከጎዳቸው ሀገራት መካከል አሜሪካንን በማስቀደም በሁለተኛ ደረጃ ላይ እንድትቀመጥ አድርጓታል።

ከዚያም ባለፈ በሀገሪቱ የወረርሽኙ ስርጭት ከፍተኛ በሆነበት ሁኔታ ሱቆች እና ምግብ ቤቶች እንደገና መከፈተቻው ተነግሯል።

የሀገሪቱ ፕሬዝዳንት ጃየር ቦልሶናሮ÷ ኮቪድ-19 “ትንሽ ጉንፋን” ነው ብለው በመጥራት ለበሽታው በሰጡት ምላሽ በሀገር ውስጥ እና በውጭ ሀገራት ትችት ሲሰነዘርባቸው መቆየቱ ይታወሳል።

ከዚያም ባለፈ ፕሬዝዳንት ቦልሶናሮ  የቫይረሱን ተፅእኖ ዝቅ አድርገው በማሰብ እንዲሁም በሽታውን ለመቆጣጠር የተወሰዱ እርምጃዎችንም  ኢኮኖሚውን ሊጎዱ  ይችላሉ በሚል መቃወማቸው ይነገራል።

ባለሞያዎች የቦልሶናሮ መንግስት የተቀናጀ እቅድ ስለሌለው ወረርሽኙ እንዲህ እየተስፋፋ ባለበት ሁኔታ የአካባቢ ባለስልጣናት ኢኮኖሚውን እንደገና ለማነቃቃት ትኩረት በማድረግ ላይ ናቸው በማለት ቅሬታቸውን በመግለጽ ላይ ናቸው ተብሏል።

ምንጭ፡- ቢቢሲ

#FBC
የዜና ሰዓት ሳይጠብቁ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ትኩስ እና ሰበር ዜናዎችን በፍጥነት በአጭር የፅሁፍ መልዕክት መልክ በስልክዎ ላይ እንዲደርስዎ ወደ 8111 OK ብለው ይላኩ።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.