Fana: At a Speed of Life!

በብራዚል በኮሮና ቫይረስ ምክንያት በአንድ ቀን ከፍተኛ የሟቾች ቁጥር ተመዘገበ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 25፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ብራዚል ወረርሸኙ ከተከሰተ ጀምሮ በአንድ ቀን ከፍተኛ የሟቾች ቁጥር ማስተናገዷን አስታወቀች፡፡

የሀገሪቱ የጤና ሚኒስቴር እንዳስታወቀው በአንድ ቀን ብቻ በቫይረሱ አማካኝነት 1 ሺህ 910 ሰዎች ለህልፈት ተዳርገዋል፡፡

በሃገሪቱ ለሁለት ተከታታይ ቀናት ከፍተኛ የሟቾች ቁጥር ሲመዘገብ ከ71 ሺህ በላይ ሰዎች ደግሞ በቫይረሱ ተይዘዋል፡፡

እንደ ጆን ሆፕኪንስ መረጃ ከሆነ በቫይረሱ አማካኝነት እስካሁን ከ275 ሺህ በላይ ብራዚላውያን ህይወታቸውን አጥተዋል፡፡

ይህም በወረርሽኑኙ ከተጠቁ የዓለም ሃገራት መካከል ብራዚልን ከአሜሪካ በመቀጠል ሁለተኛ ያደርጋታል፡፡

ደቡብ አሜሪካዊቷ ሃገር እስካሁን ከ10 ነጥብ 6 ሚሊየን በላይ ዜጎቿ ኮሮና ቫይረስ ተገኝቶባቸዋል፡፡

የሀገሪቱ ፕሬዚዳንት ጃዬር ቦልሶናሮ ለወረርሸኙ ተገቢውን ትኩረት አልሰጡም በሚል ቅሬታ እየቀረበባቸው ይገኛል፡፡

ከቅሬታ አቅራቢዎቹ መካከል የሳኦ ፖሎ ገዢ ጆዓኦ ዶሪያ አንዱ ሲሆን በፕሬዚዳንቱ “ዳተኝነት” ምክንያት በየዕለቱ ከ1 ሺህ በላይ ሰዎች ህይወታቸውን እያጡ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

የሳኦ ፖሎ ገዢ ከፍተኛ የሟቾች ቁጥር መመዝገቡን ተከትሎ በከተማዋ ለሁለት ሳምንት የሚቆይ ከፊል ክልከላዎችን አሳልፈዋል፡፡

ሆኖም ፕሬዚዳንቱ ክልከላዎችን በሚያውጁ ገዢዎችና ከንቲባዎች ላይ እርምጃ እንደሚወስዱ ተናግረዋል፡፡

ምንጭ፡-አልጀዚራ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡-https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.