Fana: At a Speed of Life!

በኒጀር በታጣቂዎች በተፈጸመ ጥቃት የእርዳታ ሰራተኞችን ጨምሮ የ8 ሰዎች ህይወት አለፈ

አዲስ አበባ፣ ነሀሴ 4፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በኒጀር ታጣቂዎች በፈፀሙት ጥቃት የፈረንሳይ ዜግነት ያላቸው የእርዳታ ሰራተኞችን ጨምሮ የ8 ሰዎች ህይወት ማለፉ ተገለፀ።

በጥቃቱ ህይወታቸው ካለፈው ውስጥ 6 ሰዎች የፈረንሳይ ዜጎች ሲሆኑ፥ ቀሪዎቹ ደግሞ የኒጀር ዜግነት ያላቸው አሽከርካሪ እና አስጎብኚዎች ናቸው ተብሏል።

የኒጀር ቲላቤሪ ክልል አስተዳዳሪ ታጅዲን ኢብራሂም ጥቃቱን አስመልክቶ በሰጡት መግለጫ፥ ታጣቂዎቹ በሞተር ሳይክል ጥቃቱን መፈፀማቸውን አስታውቀዋል።

በጥቃቱ ህይወታቸው ያለፈው ሰዎች ጎብኚዎች በብዛት የቀጭኔ መንጋ ለማየት ወደሚጓዙበት ኮሬ ክልል ውስጥ እያሉ ጥቃቱ እንደተፈፀመባቸውም አረጋግጠዋል።

የፈረንሳይ ፕሬዚዳንት ፅህፈት ቤትም በኒጀር በተፈፀመው ጥቃት የፈረንሳይ ዜጎች ህይወት ማለፉን አረጋግጧል።

የፈረንሳዩ ፕሬዚዳንት ኢማኑኤል ማክሮን ከኒጀሩ ፕሬዚዳንት መሃሙዱ ኢሶፉ ጋር በጉዳዩ ዙሪያ በስልክ መነጋገራቸውም ነው የተገለፀው።

የኒጀር የመከላከያ ሚኒስትር ኢሶፉ ካታምቤ ቀደም ብለው በሰጡት መግለጫ ህይወታቸው ያለፈው ሰዎች ጎብኚዎች መሆናቸው ገልጸው የነበረ ሲሆን፥ በኋላ ላይ ግን በዓለም አቀፍ የእርዳታ ድርጅት ውስጥ የሚሰሩ የፈረንሳይ ዜጎች መሆናቸውን አረጋግጠዋል።

ምንጭ፦ bbc.com

#FBC

የዜና ሰዓት ሳይጠብቁ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ትኩስ እና ሰበር ዜናዎችን በፍጥነት በአጭር የፅሁፍ መልዕክት መልክ በስልክዎ ላይ እንዲደርስዎ ወደ 8111 OK ብለው ይላኩ።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.