Fana: At a Speed of Life!

በአለም በኮሮናቫይረስ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 100 ሚሊየን አለፈ

አዲስ አበባ፣ ጥር 18፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ)በአለም ዙሪያ በኮሮናቫይረስ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 100 ሚሊየን ማለፉ ተሰምቷል፡፡

እስካሁን በአለም አቀፍ ደረጃ በኮቪድ-19 የተያዙ ሰዎች ቁጥር ከ100 ሚሊየን 286 ሺህ 700 በላይ ሆኗል፡፡

በቫይረሱ ሳቢያ ለህልፈት የተዳረጉ ሰዎች ቁጥርም 2 ሚሊየን 149 ሺህ 496 ደርሷል፡፡

በቫይረሱ የተያዙ ዜጎቿ ቁጥር ከ25 ሚሊየን በላይ የሆነባት አሜሪካን ጨምሮ ህንድ፣ ብራዚል፣ ሩሲያ እና ብሪታኒያ ከፍተኛ ተጽዕኖ ውስጥ የወደቁ አገራት መሆናቸው ይጠቀሳል፡፡
በአንጻሩ ከቫይረሱ ያገገሙ ሰዎች ቁጥር ከ72 ሚሊየን 313 ሺህ 600 በላይ ደርሷል፡፡

ምንጭ፡- ዎርልድ ኦ ሜትር

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.