Fana: At a Speed of Life!

በአማራ ክልል በተጀመሩ የመስኖ ፕሮጀክቶችና ግድቦች ዙሪያ ውይይት ተካሄደ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 9፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በአማራ ክልል በተጀመሩ የመስኖ ፕሮጀክቶችና ግድቦች ዙሪያ በባህርዳር ውይይት ተካሄደ፡፡
 
በውይይቱ ላይ የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ዶክተር ፋንታ ማንደፍሮ፣ የክልሉ የካቢኔ አባላትና የውሃ፣ መስኖና ኢነርጂ ሚኒስትሩ ዶክተር ስለሺ በቀለ ተገኝተዋል።
 
ምክትል ርዕሰ መስተዳድሩ ዶክተር ፋንታ ማንደፍሮ ኢትዮጵያ የብዙ ተፋሰስ ባለቤት መሆኗን አንስተው በክልሉ ያለው አቅም ደግሞ ትልቅ መሆኑን አስረድተዋል፡፡
 
እንዲሁም ክልሉ የመስኖ ልማቶችና ግድቦች ካሉበት ችግር እንዲወጣ ከፌደራል መንግስት ጋር በጥምረት እየተሰራ መሆኑን ጠቅሰዋል፡፡
 
በውይይቱ ላይ በአራት ዋና ዋና ተፋሰሶች ዙሪያ ምክክር ተደርጓል፡፡
 
በክልሉ አሁን ላይ ያሉት ፕሮጀክቶች ርብ፣ መገጭ፣ ቆቦ፣ ጊራና መሆናቸው ይታወቃል፡፡
 
እነዚህን ፕሮጀክቶች በተያዘው በጀት ዓመት አጠናቆ ወደ ስራ ለማስገባት ጥረት እንደሚደረግም ነው የተነሳው፡፡
 
በሳራ መኮነን
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.