Fana: At a Speed of Life!

በአባይ ተፋሰስ እና በታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ላይ መንግስትን የሚያማክር የተመራማሪዎች እና የምሁራን ጥምረት ሊመሰረት ነው

አዲስ አበባ ፣ሰኔ 17፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በአባይ ተፋሰስ፣ በህዳሴው ግድብ እና በሌሎች ጉዳዮች ላይ መንግስትን የሚያማክር የተመራማሪዎች እና የምሁራን ጥምረት ተመስርቶ በቅርቡ ስራ እንደሚጀምር የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስትር ዲኤታ ዶክተር ሳሙኤል ክፍሌ አስታወቁ።

ሚኒስትር ዲኤታው በውሃ አጠቃቀም፣ በፕሮጀክቶች እና በግድቦች አስተዳደር ዙሪያ ምርምር የሚሰሩ ማዕከላትን ያጠናከራሉ፣ አዳዲሶችንም ፈጥሮ ወደስራ ያስገባል ብለዋል፡፡

በውሃ ምርምርና በውሃ የትምህርትና ስልጠና ፕሮግራሞች ላይ የሚሰሩ ዩኒቨርሲቲዎች በበለጠ ትኩረት እንዲሰሩና ብቁ ምሁራንን እንዲያፈሩ እንደሚሰራ እና እንደ አስፈላጊነቱም አዳዲስ ፕሮግራሞች ተከፍተው ወደስራ እንደሚገቡ ገልፀዋል።

ዶክተር ሳሙኤል ኢትዮጵያ በሌሎች ማስፈራሪያ ልማትን ከማካሄድና ብርሃንን ከማየት ወደኋላ እንደማትል ጠቅሰው ይህን መብቷን እንደምታስከብር አስረድተዋል።

በግድቡ ላይ ሁላችንም ዜጎች ልዩነት የለንም ያሉት ሚኒስትር ዲኤታው ታላቁ የህዳሴ ግድብ በሀገራችን መሬት፣ ከወንዞቻችን በሚመነጭ ውሃ፣ ከዜጎቻችን መቀነትና ኪስ በሚገኝ ገንዘብ ከድህነት ለመላቀቅ የምንገነባው ግድብ ነው ብለዋል፡፡

የትምህርትና ስልጠና ማህበረሰቡ ሀገር ከድህነት ተላቃ ወደ ብልፅግና የምታደርገውን ጉዞ በሚያስፈልገው ሁሉ እንደሚደግፍም ተናግረዋል።

በተለያዩ ሃገራት የሚገኙ ኢትዮጵያውያን፣ ትውልደ ኢትዮጵያውያንና የኢትዮጵያ ወዳጆች ሀገራችን የተፈጥሮ ሃብቷን ለመጠቀም ያላትን መብት በመረዳት ከዚህ በተቃራኒው የቆሙትን የውስጥ ይሁን የውጭ ሃይሎች በማውገዝና የኢትዮጵያን አቋም በማስረዳት ድጋፋቸውን አጠናክረው እንዲቀጥሉም ጥሪ አቅርበዋል፡፡

#FBC

የዜና ሰዓት ሳይጠብቁ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ትኩስ እና ሰበር ዜናዎችን በፍጥነት በአጭር የፅሁፍ መልዕክት መልክ በስልክዎ ላይ እንዲደርስዎ ወደ 8111 OK ብለው ይላኩ።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.