Fana: At a Speed of Life!

በከተሞች ፍትሐዊ የልማት ስርጭት እንዲኖር ተግተን እንሰራለን – ም/ርዕሰ መስተዳድር ነጋሽ ዋጌሾ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 5፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በክልሉ ብዝሃ ዋና ከተሞችና ሌሎች ተደራሽ በሆኑ ከተሞች ውስጥ ፍትሐዊ የልማት ስርጭትና የኢኮኖሚ እንቅስቃሴ እንዲኖር ተግተን እንሠራለን ሲሉ የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ነጋሽ ዋጌሾ ተናገሩ፡፡

ምክትል ርዕሰ መስተዳድሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት ጽሑፍ÷ “የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልላዊ መንግሥት በክልሉ ሕዝቦች መካከል አብሮነትና አንድነትን በማጎልበት ፍትሐዊ ተጠቃሚነትን እውን በማድረግ የጋራ ራዕይ የሆነውን ብልጽግና ለማረጋገጥ የሚያግዙ ተግባራትን እያከናወነ ነው ብለዋል፡፡

ብዝሃነት ከልዩነት ይልቅ ለጋራ ልማትና አንድነት አቅም መሆኑን በመረዳት ፍትሐዊ ልማትና መልካም አስተዳደር በክልሉ ውስጥ እንዲሰፍን እየተወሰደ ያለው እርምጃ አበረታች መሆኑንም ገልጸዋል፡፡

አንኳር የሆኑ የሕዝቡ አዳጊ ፍላጎቶች እውቅና ተሰጥቷቸው ምላሽ እንዲያገኙ የክልሉ ሕዝቦች በመረጧቸው ተወካዮቻቸው በኩል የሰጡት ድጋፍና ያሳዩት በሳል አመራር ተደማሪ አቅም ይሆናልም ነው ያሉት።

በክልሉ ብዝሃ ዋና ከተሞችና ሌሎች ተደራሽ በሆኑ ከተሞች ውስጥ ፍትሐዊ የልማት ስርጭትና የኢኮኖሚ እንቅስቃሴ እንዲኖር ተግተን እንሠራለን ሲሉም ገልጸዋል፡፡

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.