Fana: At a Speed of Life!

የዳያስፖራ አባላት ለ’ጽዱ ኢትዮጵያ’ ንቅናቄ ድጋፍ አደረጉ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 2፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በአሜሪካ የሚኖሩ የዳያስፖራ አባላት ለ’ጽዱ ኢትዮጵያ’ ንቅናቄ በአይነት እና በገንዘብ ድጋፍ አድርገዋል፡፡

ዋሽንግተን ዲሲ የሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ ባዘጋጀው የ‘ጽዱ ኢትዮጵያ’ የድጋፍ ማሰባሰቢያ የበይነ መረብ መድረክ ላይ ነው ኢትዮጵያውያኑ እና ትውልደ ኢትዮጵያውያንኑ ድጋፉን ያደረጉት፡፡

በዚህም በአጠቃላይ በዓይነት 18 ሚሊየን ብር የሚገመቱ 12 መጸዳጃ ቤቶችን ለመስራት ቃል የተገባ ሲሆን÷ በጥሬ ገንዘብ ደግሞ 17 ሺህ 945 ዶላር እንዲሁም 74 ሺህ ብር ድጋፍ ተደርጓል፡፡

በዚህ ወቅት በአሜሪካ የኢትዮጵያ ልዩ መልዕክተኛ እና ባለሙሉ ሥልጣን አምባሳደር ስለሺ በቀለ (ዶ/ር ኢ/ር) ÷ንቅናቄው የአፍሪካ ህብረት መቀመጫ የሆነችውን አዲስ አበባን ጽዱ፣ አረንጓዴ እና ለነዋሪዎቿ ምቹ ማድረግን ያለመ ነው ብለዋል።

በተጨማሪም ንቅናቄው ለአካባቢ ንጽህና እና ጤና ከሚያበረክተው አስተዋጽኦ በተጨማሪ ለሴቶችና ወጣቶች የስራ ዕድል የሚፈጥር መሆኑንም በንግግራቸው ጠቅሰው ኢትዮጵያውያን እና ትውልድ ኢትዮጵያውያን ድጋፍ እንዲያደርጉ ጠይቀዋል።

በኤምባሲው የሚገኙ ዲፕሎማቶች እና ሰራተኞችም ለንቅናቄው ከደመወዛቸው መለገሳቸውን ከኤምባሲው ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.