Fana: At a Speed of Life!

በደቡብ ሱዳን በሳምንቱ መጨረሻ በተፈጠረ ግጭት የ70 ሰወች ህይወት አልፏል

አዲስ አበባ፣ ነሀሴ 6፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ)በደቡብ ሱዳን በሳምንቱ መጨረሻ በጦር ሰራዊቱ እና ሲቪሎች መካከል በተፈጠረ ግጭት የ70 ሰወች ህይወት ማለፉን የተባበሩት መንግስታት ድርጅት አስታውቋል፡፡

በሃገሪቱ ሰሜን-ማዕከላዊ ዋራፕ ግዛት በደቡብ ሱዳን ጦር እና የታጠቁ ሲቪሎች በተፈጠረው ግጭት ህይወታቸው ካለፈው በተጨማሪ በርካቶች ቆስለዋል ነው የተባለው፡፡

ግጭቱ በአካባቢው ታጣቂዎችን ትጥቅ ለማስፈታት በተጀመረ እንቅስቃሴ መግባባት አለመፈጠሩን ተከትሎ የተፈጠረ መሆኑም ነው የተነገረው፡፡

በስፍራው የሚገኙ ታጣቂዎችም በአቅራቢያው በሚገኝ የጦር ሰፈር ላይ ጥቃት ሰንዝረዋል ተብሏል፡፡

የትጥቅ መፍታት ሂደቱ በቅርቡ የደቡብ ሱዳን ፕሬዚዳንት ሳልቫ ኪር እና ምክትላቸው ሪክ ማቻር የደረሱት የሰላም ስምምነት አካል መሆኑም ተገልጿል፡፡

ደቡብ ሱዳን በፈረንጆቹ 2011 ከሱዳን ተነጥላ ሉዓላዊ ሃገር ከሆነች ወዲህ የእርስ በርስ ጦርነት ውስጥ ገብታለች፡፡

ምንጭ፡-አልጀዚራ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.