Fana: At a Speed of Life!

በደቡብ አሜሪካ በኮሮና ቫይረስ የሞቱ ሰዎች ቁጥር ከ50 ሺህ አልፏል

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 24 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) በደቡብ አሜሪካ በኮሮና ቫይረስ የሞቱ ሰዎች ቁጥር ከ50 ሺህ አልፏል።

በአህጉሩ በኮሮና ቫይረስ የተያዙ ሰዎች ቁጥር ወደ 1 ሚሊየን መጠጋቱም ነው የተነገረው።

ብራዚል፣ ቺሊ እና ፔሩ ቫይረሱ በስፋት የተንሰራፋባቸው ሃገራት ናቸው።

ብራዚል 33 ሺህ 274 አዲስ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎችን ስታስመዘግብ ይህም በአጠቃላይ በሃገሪቱ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎችን ቁጥር ወደ 514 ሺህ 992 አድርሶታል።

እንደ ሃገሪቱ የጤና ሚኒስቴር መረጃ በ24 ሰዓታት ውስጥ የተመዘገበውን 956 የሞት ቁጥርን ጨምሮ የሟቾች ቁጥር ወደ 29 ሺህ 341 ከፍ ብሏል።

በፔሩ 164 ሺህ 476 ሰዎች በቫይረሱ ሲያዙ 4 ሺህ 506 ሰዎች ለህልፈት ተዳርገዋል።

በቺሊ ደግሞ 99 ሺህ 688 ሰዎች በቫይረሱ ተይዘው 1 ሺህ 54 ሰዎች ለህልት ተዳርገዋል ነው የተባለው።

 

ምንጭ፦ አልጀዚራ

 

 

 

 

 

 

 

 

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.