Fana: At a Speed of Life!

በደቡብ አፍሪካ የኦሚክሮን ቫይረስ ስርጭት መቀነሱን የሀገሪቱ ተመራማሪዎች አስታወቁ

አዲስ አበባ፣ታህሳስ 14፣ 2014 (ኤፍ ቢሲ) በደቡብ አፍሪካ የኦሚክሮን ቫይረስ ከፍተኛ ስርጭት መጠን እየቀነሰ መሆኑን የሀገሪቱ ተመራማሪዎች አስታውቀዋል።
የሃገሪቱ የጤና ባለሙያ ማርታ ኑኔስ፥ በደቡብ አፍሪካ አራተኛው የኮቪድ-19 ኦሚክሮን ቫይረስ በሽታ በፍተኛ ደረጃ ተሰራጭቶ እንደነበር እና ስርጭቱንም ለወራት በተደረገ ከፍተኛ ርብርብ መቀነስ መቻሉን ገልፀዋል፡፡
የዊትዋተር ስራንድ ዩኒቨርሲቲ አካዳሚክ ተመራማሪዎች በበኩላቸው፥ ሀገሪቱ ያጋጠማት የአጭር ጊዜ ከባድ ወረርሽኝ ነበር፤ የአራተኛውን የኮሮና ቫይረስ ስርጭት ማዕበልን እንዳለፈች አመላካች መረጃዎች መኖራቸውን መናገር ይቻላል ብለዋል።
በህዳር ወር የመጨረሻ ሳምንት በቀናት ምርመራ በርካታ ሰዎች በሽታው ይገኝባቸው እንደነበር፥ ነገር ግን ስርጭቱን ለመግታት ከፍተኛ ርብርብ በመደረጉ የማዕበሉን መግታት ተችሏል ነው ያሉት፡፡
በአሁኑ ሰዓት የኦሚክሮን ተህዋሲ በመላው ዓለም በፍጥነት እየተሰራጨ ሲሆን፥ የአለም ጤና ድርጅትም የቫይረሱን ስርጭት ለመግታት ሀገራት እንዲረባረቡ ጥሪ ማቅረቡ የሚታወስ ነው፡፡
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.