Fana: At a Speed of Life!

በጅግጅጋ ለሚገነባው የካህ ትምህርት ቤት የመሠረት ድንጋይ ተቀመጠ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 8፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሽመልስ አብዲሳ እና የሶማሌ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሙስጠፌ መሐመድ በጅግጅጋ ከተማ ለሚገነባዉ ዘመናዊ ትምህርት ቤት የመሠረት ድንጋይ አስቀመጡ።
የዚህ ዘመናዊ ትምህርት ቤት ወጪ በኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት የሚሸፈን ይሆናል ተብሏል።
በመሠረት ድንጋይ ማስቀመጥ ስነ ስርዓቱ ላይ አቶ ሽመልስ እንደገለፁት÷ የትምህርት ቤቱ ግንባታ ዛሬውኑ የሚጀመር መሆኑን ጠቅሰዉ ግንባታው በ7ወር ጊዜ ውስጥ እንደሚጠናቀቅ ተናግረዋል።
አቶ ሙስጠፌ በበኩላቸው÷ የሶማሌ እና የኦሮሞ ህዝብ ወንድማማች ናቸው፤ የትምህርት ቤቱ ግንባታ የሁለቱን ህዝብ ግንኙነት ያሳድጋል ብለዋል ሲል የሶማሌ ክልል ብዙኃን መገናኛ ድርጅት ዘግቧል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.