Fana: At a Speed of Life!

በጤናው ዘርፍ የተሰማሩ ባለሙያዎችና ተመራማሪዎች እያደረጉ ያሉትን ከፍተኛ አስተዋጽኦ አጠናክረው እንዲቀጥሉ ጥሪ ቀረበ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 25፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የኦሮሚያ ጤና ቢሮ የመጀመሪያው የጥናት ዓመታዊ ጉባዔ ተካሄደ፡፡

በመድረኩም የጤና ሚኒስትር ዴኤታ ዶክተር ደረጄ ዱጉማን ጨምሮ የተለያዩ የፌደራልና የክልሉ የጤና ዘርፍ የሥራ አመራሮች፣ አባ ገዳዎች፣ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት እና የተለያዩ ባለድርሻ አካላት ተገኝተዋል።

የጤና ሚኒስትር ዴኤታ ዶክተር ደረጄ ዱጉማ በመድረኩ ላይ ባስተላለፉት መልክት ፥ ሀገራችን በጦርነት፣ ድርቅ፣ ኮቪድ-19፣ እና ዘርፈ ብዙ ችግሮች ውስጥ ባለችበት በዚህ ወቅት በጤናው ዘርፍ የህብረተሰቡን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ሰፊ ጥረቶች እየተደረጉ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

የጤና ስራ በጥናትና ምርምር መደገፍ ሰላለበት በዘርፉ የተሰማሩ ባለሙያዎችና ተመራማሪዎች እያደረጉ ያሉትን ከፍተኛ አስተዋጽኦ አጠናክረው እንዲቀጥሉ ጠይቀዋል።

የኦሮሚያ ጤና ቢሮ ምክትል ኃላፊ አቶ አበራ ቦቶሬ በበኩላቸው ፥ በክልሉ በጤናው ዘርፍ የተሰሩ የምርምር ውጤቶች ለጤናው ሴክተር ዕቅድ እና ውሳኔ ሰጭነት እንዲውል በማድረግ የማይበገር የጤና ስርዓት መገንባት የመድረኩ ዋና ዓላማው እንደሆነ ገልጸዋል።

ለሁለት ቀናት በሚቆየው በዚህ መድረክ በክልሉ ጤናን መሰረት አድርገው 62 የምርምር ውጤቶቸ በመድረኩ እንደሚቀርቡም ምክትል ኃላፊው ተናግረዋል።

በኦሮሚያ ጤና ቢሮ እና በጅማ ዩኒቨርሲቲ በጋራ ያዘጋጁት የመጀመሪያ የሆነው የጥናትና ምርምር ዓመታዊ ጉባዔ መሆኑን ከሚኒስቴሩ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.