Fana: At a Speed of Life!

በዓለም አቀፍ ደረጃ በጥቂት ቀናት ውስጥ በኮሮና ወረርሽኝ  የተያዙ ሰዎች ቁጥር ወደ 1 ሚሊዮን ከፍ ይላል-የአለም የጤና ድርጅት

አዲስ አበባ፣መጋቢት 24፣2012(ኤፍ.ቢ.ሲ) በአለም አቀፍ ደረጃ በሚቀጥሉት ጥቂት ቀናት ውስጥ በኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ  የሚያዙ ሰዎች ቁጥር 1 ሚሊየን ይሆናሉ ሲል  የአለም የጤና ድርጅት አስታወቀ፡፡

ከዚያም ባለፈ  በቅርብ ቀናት ውስጥ በወረርሽኙ  ለህልፈት የሚዳረጉት ሰዎች ቁጥር ወደ 50 ሺህ ከፍ እንደሚልም  የአለም የጤና ድርጅት ዳይሬክተር  ዶክተር ቴድሮስ አድሃኖም ገልጸዋል፡፡

በአሁኑ ወቅት በዓለም አቀፍ ደረጅ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 932 ሺህ 605 መድረሱን  ተገልጿል፡፡

ከዚህ ውስጥም አሜሪካ 216 ሺህ በላይ የሚሆኑ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎችን በማስመዝገብ ቀዳሚ ናትም ነው የተባለው፡፡

በሌላ በኩል በአሁኑ ወቅት በዓለም አቀፍ ደረጃ በቫይረሱ ሳቢያ ህይወታቸው ያለፉ ሰዎች ቁጥር 46 ሺህ 800 መድረሱን ጆንስ ሆፕኪንስ ዩኒቨርሲቲ አስታውቋል።

በአሜሪካ በአንድ ቀን ውስጥ  ብቻ 25 ሺህ ሰዎች በቫይረሱ የተያዙ ሲሆን÷ 884  ሰዎች  በቫይረሱ ምክንያት ህወታቸው አልፏል፡፡

ለህልፈት ከተዳረጉት ሰዎች መካከል የስድስት ሳምንት ዕድሜ ያለው ህፃን  ይገኝበታልም ነው የተባለው፡፡

የኒው ዮርክ ከተማ  በቫይረሱ ክፉኛ የተጎዳች ሲሆን 1 ሺህ 300 ሰዎች ለህልፈት ተዳርገዋል ፡፡

የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ መስፋፋትን ተከትሎም ከ75 በመቶ በላይ የሚሆነው የአሜሪካ ህዝብ ከቤት እንዳይወጡ ትእዛዝ ተላልፏል፡፡

ምንጭ፡-ቢ.ቢ.ሲ  እና ሮይተርስ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.