Fana: At a Speed of Life!

በፓኪስታን ኩዌታ በአይ ኤስ በተፈፀመ የቦምብ ጥቃት የሟቾች ቁጥር 15 ደረሰ

አዲስ አበባ፣ ጥር 2፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በፓኪስታን ደቡብ ምእራብ ኩዌታ ከተማ በመስጊድ ላይ በተፈፀመ የቦብም ጥቃት የሞቱ ሰዎች ቁጥር 15 መድረሱን ፖሊስ አስታወቀ።

በአርብ ፀሎት ላይ በነበሩ ሰዎች ላይ በተፈፀመው የቦምብ ጥቃቱ ከሞቱት ሰዎች በተጨማሪም ከ20 በላይ ሰዎች ላይ የተለያየ መጠን ያለው ጉዳት መድረሱንም ነው የገለፀው።

በመስጊድ ላይ ለተፈፀመው ጥቃትም በአካባቢው የሚንቀሳቀሰው የአሸባሪው ኢስላሚክ ስቴት (አይ.ኤስ) ቡድን ኃላፊነት መውሰዱ ተነገሯል።

በሽብር ጥቃቱ በአፍጋኒስታን የሚንቀሳቀሰው የታሊባን ቡድን አመራሮች ተገድለዋል ቢባልም፤ ታሊባን ግን አመራሮቼ ላይ ጉዳት አልደረሰም ሲል አስተባብሏል።

ምንጭ፦ www.reuters.com

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.