Fana: At a Speed of Life!

ቦርዱ ለ6 ፓርቲዎች የምዝገባና የሀጋዊ ሰውነት ማረጋገጫ የምስክር ወረቀት ሰጠ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 10፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ለስድስት የፖለቲካ ፓርቲዎች የምዝገባ እና የሀጋዊ ሰውነት ማረጋገጫ የምስክር ወረቀት ሰጠ።

በዚህም መሰረት የምዝገባ እና የሀጋዊ ሰውነት ማረጋገጫ የምስክር ወረቀት የተሰጣቸው፦

  • ሕብር ኢትዮጵያ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ
  • መላው አማራ ህዝብ ፓርቲ
  • ነጻነትና ሰላም ለኢትዮጵያ ህብረት ፓርቲ
  • የኢትዮጵያ ዜጎች ለማህበራዊ ፍትህ ( ኢዜማ)
  • አፋር ነጻ አውጪ ግንባር ፓርቲ ( አነግፓ) እና
  • የቦሮ ዴሞክራቲክ ፓርቲ ናቸው።

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የምዝገባ እውቅና ከተሰጣቸው በተጨማሪ ለሌሎች 11 ፓርቲዎች ጊዜያዊ እውቅና (የሶስት ወር) መስጠቱንም አስታውቋል።

በዚህም መሰረት

  • ኤጄቲማ ፌዴራሊስት ፓርቲ (ኤፌፓ)
  • ሱማሌ ፌደራሊስት ፓርቲ
  • የካፋ ሀዝቦች ዴሞክራሲያዊ ሀብረት (ካህዴህ)
  • የፊንፊኔ ህዝቦች ለፍትህ እና ለዴሞክራሲ ፓርቲ (ፊህዲ)
  • የራያ ራዩማ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ
  • ለኅብሀር ለዴሞክራሲና ለነፃነት ፓርቲ (ኅዴነፓ)
  • ለሲዳማ አንድነት ፓርቲ (ሲአፓ)
  • ኢትዮጵያዊ ሀገር አቀፍ ፓርቲ
  • ሶማሌ ብሄራዊ ፓርቲ (ሶብፓ)
  • የኢትዮጵያ አንድነት አርበኞች ግንባር እና
  • የወለኔ አርሶ አደር ህብረት ጊዜያዊ እውቅና እንደተሰጣቸው ነው ቦርዱ ያስታወቀው።
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.