Fana: At a Speed of Life!

ትራምፕና ባይደን ሁለተኛውን ፕሬዚዳንታዊ ክርክር በቨርቹዋል እንዲያካሂዱ ቢወሰንም ፕሬዚዳንቱ እንደማይገኙ አሳውቀዋል

አዲስ አበባ፣ መስከረም 28፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ እና በዲሞክራቱ እጩ ጆ ባይደን መካከል የሚካሄደው ሁለተኛው ፕሬዚዳንታዊ ክርክር በቨርቹዋል እንዲያካሂዱ ቢወሰንም ትራምፕ እንደማይሳተፉ አሳውቀዋል፡፡
 
ቀደም ብሎ ውሳኔውን የፕሬዚዳንታዊ ክርክሩ ኮሚሽን ነበር ያሳለፈው፡፡
 
ኮሚሽኑ ውሳኔውን ያሳለፈው ፕሬዚዳንት ትራምፕ ባለፈው ሳምንት በኮሮና ቫይረስ መያዛቸውን ተከትሎ ነው፡፡
 
ትራምፕ ዘግይቶ ይፋ በሆነ ዜና በቨርቹዋ ክርክሩ እንደማይገኙ አሳውቀዋል፡፡
 
እንዲሁም ጊዜዬንም አላጠፋም ሲሉ ተደምጠዋል፡፡
 
በፕሬዚዳንት ትራምና በጆ ባይደን መካከል ይደረጋል ተብሎ የታሰበው ሁለተኛው ክርክር በሚቀጥለው ሳምንት እንዲካሄድ ነበር የተወሰነው፡፡
 
ትራምፕ ሚያሚ ላይ የፊት ለፊት ክርክር ለማድረግ ቀደም ብሎ ዝግጁ መሆናቸውን ቢገልጹም ባይደን የህክምና ባለሙያዎች የሚሉትን እጠብቃለሁ ሲሉ ተደምጠው ነበር፡፡
 
የፕሬዚዳንቱ የግል ሐኪም ትራምፕ ከ24 ሰዓታት በላይ ምልክት ያለማሳየታቸውንምማሳወቁን ቢቢሲ ዘግቧል፡፡

ትናንት ምሽት ደግሞ ምክትል ፕሬዚዳንት ማይክ ፔንስና የዲሞክራቷ እጩ ሴናተር ካሚላ ሃሪስ የፊት ለፊት ውይይት አድርገዋል፡፡

 
ባለፈው ሳምንት ትራምፕና ባይደን በዘለፋ የተሞላ ነበር የተባለውን የመጀመሪያ ክርክራቸውን በፎክስ ኒውሱ አዘጋጅ ክሪስ ዋላስ አማካኝነት ማካሄዳቸው የሚታወስ ነው፡፡
 
በትራምፕና በባይደን መካከል የሚደረገው የ2020 የአሜሪካ ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ ሊካሄድ 25 ቀናት ብቻ ቀርተውታል፡፡
 
 
 

በአብርሃም ፈቀደ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.