Fana: At a Speed of Life!

ቻይና ኤል-ኤስ ኤ አር የተሰኘ ሳተላይት ወደ ህዋ አመጠቀች

አዲስ አበባ፣ ጥር 18፣ 2014 (ኤፍ ቢሲ) ቻይና ለመሬት ምርምር አገልግሎት የሚውል ኤል-ኤስ ኤ አር የተሰኘ ሳተላይት ወደ ህዋ ማምጠቋን አስታውቃለች።

ሳተላይቱ ዛሬ ከቀኑ 7፡44 ላይ በሰሜን ምዕራብ ቻይና ከሚገኘው የጂዩኳን ሳተላይት ማዕከል ነው ወደ ጠፈር የተላከው፡፡

ይህ በአገሪቱ ትልቁ የመሬት ምልከታ ሳተላይት ምህዋር ላይ በሚቆይበት ጊዜ የሀገሪቱን የከርሰ ምድር አቅም ለመለካት የሚያስችሉ ወሳኝ መረጃዎችን ይልካል ተብሎ ይጠበቃል፡፡

የሳተላይቱ ክብደት 3 ነጥብ 2 ቶን የሚመዝን ሲሆን፥ ከ33 ካሬ ሜትር በላይ ስፋት እንዳለው የሲ ጅ ቲ ኤን ዘገባ ያመላክታል።

ሳተላይቱ ቻይና ያካሄደቻቸውን በርካታ የመሬት ጥናቶች ትክክለኛነት ማረጋገጥ የሚያስችል ሲሆን፥ ሳይንቲስቶች በደን የተሸፈኑ ቦታዎችን ላይ የበለጠ ምርምር ለማድረግ ያግዛቸዋል ተብሏል፡፡

የሻንጋይ የጠፈር በረራ ቴክኖሎጂ አካዳሚ ባወጣው መግለጫ የሳተላይቱ አሠራር ቻይና በሌሎች አገሮች በሚወጡ የራዳር መረጃዎች ላይ ያላትን ጥገኝነት በእጅጉ ሊቀንሰው እንደሚችል አስታውቋል።

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.