Fana: At a Speed of Life!

አሸባሪውን ህወሃትን ለመመከት ተመራቂዎች የተሻለ አቅም ይፈጥራሉ- ሌተናል ጄነራል አስራት ዴኔሮ

አዲስ አበባ ፣ ሐምሌ 17፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በኢፌዴሪ መከላከያ የሰላም ማስከበር ማዕከል የሁርሶ ኮንቲንጀንት ማሰልጠኛ መሰረታዊ ወታደሮችን በ2ኛ ዙር አስመረቀ፡፡
የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት ከህዝቡ አብራክ የወጣ ማንኛውንም የጭቆና ቀንበር ለመስበር ቁርጠኛ የሆነ መሆኑን የምድር ኃይል ጠቅላይ መምሪያ ዋና አዛዥ ሌተናል ጄነራል አስራት ዴኔሮ ተናግረዋል።
ኢትዮጵያ ከውስጥና ከውጪ ሀይሎች የተለያዩ ትንኮሳዎች በሚቃጣባት ወቅት ይህን ሰራዊት ማስመረቅ በተለይም አሸባሪው የህወሃት ቡድን የመጨረሻ አቅሙን አሟጦ ኢትዮጵያን የማፈራረስ የሞት ሽረት ላይ ባለበት ወቅት መመረቃቸው የሀገሪቱን ህልውና ለማስጠበቅ የተዘጋጃችሁ ብርቅዬ የኢትዮጵያ ልጆች ናችሁ ብለዋል።
በዚህ ወቅት በርካታ መሰረታዊ ወታደሮች መሰልጠናቸው ሀገሪቱ የአሸባሪው ህወሃት ሀገር የማፍረስ ተልዕኮ ለመመከትና የሀገሪቱን መሰረተ ልማት ጥበቃ ይበልጥ ለማጠናከር የተሻለ አቅም ይፈጥራሉ ተብሏል።
6ኛው ሀገራዊ ምርጫ በሰላም በተጠናቀቀበት እና 2ኛ ዙር የህዳሴ ግድብ ሙሌት በስኬት በተጠናቀቀበት ወቅት በመመረቃቸው የመከላከያ ሰራዊቱ ጋር በመቀላቀል ተልዕኳቸውን የሚወጡ ለቀጣይ ድርብርብ ድል የተዘጋጁ መሆናቸውን የሁርሶ ኮንቲንጀንት ማሰልጠኛ ት/ቤት አዛዥ ኮሎኔል አዲሱ ተርፌሳ መግለጻቸውን ኢቢሲ ዘግቧል።
ተመራቂ መሰረታዊ ወታደሮች የኢትዮጵያን ሉዓላዊነትና የዜጎችን ደህንነት ለማስጠበቅ በቁርጠኝነት የሚሰጠንን ተልዕኮ እንወጣለን ብለዋል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.