Fana: At a Speed of Life!

አየር መንገዱ ከአፍሪካ ግዙፍ 10 አየር መንገዶች ቀዳሚው ሆኗል

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 19፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከአፍሪካ ግዙፍ አየር መንገዶች አሁንም በቀዳሚነት ተቀምጧል።

እንደ አፍሪካ ሎጂስቲክስ ዶት ኮም ዘገባ አየር መንገዱ በሚሰጠው አገልግሎት አሁንም ከአፍሪካ ቀዳሚ ሆኗል።

አየር መንገዱ በመንገደኞች ብዛት፣ በመዳረሻ ብዛትና በገቢ የአህጉሪቱ ቀዳሚ አየር መንገድ ተብሏል።

ከዚህ ባለፈም አየር መንገዱ ዓለም ላይ 4ኛው ግዙፍ አየር መንገድ መሆኑንም ዘገባው አመላክቷል።

በፈረንጆቹ 2019ም አየር መንገዱ ከ13 ነጥብ 3 ሚሊየን በላይ መንገደኞች አገልግሎት መስጠቱም ተገልጿል።

ከኢትዮጵያ አየር መንገድ ቀጥሎ የግብጹ ኢጅፕት ኤርላይንስ፣ የሞሮኮ፣ አልጀሪያ፣ መቀመጫውን ደቡብ አፍሪካ ያደረገው ኮሜር አየር መንገድ፣ የኬንያ አየር መንገድ፣ የደቡብ አፍሪካ፣ ቱኒዚያ፣ እንዲሁም መቀመጫቸውን ደቡብ አፍሪካ ያደረጉት ማንጎ እና ፍሊሳፍ የግል አየር መንገዶች የአህጉሪቱ ቀዳሚ 10 አየር መንገዶች ውስጥ ተካተዋል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.