Fana: At a Speed of Life!

አፍሪካ በፈረንጆቹ 2030 ረሃብን ለማጥፋት በሚያስችል መንገድ ላይ አይደለችም- ፋኦ

አዲስ አበባ ፣ የካቲት 26 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) አፍሪካ በፈረንጆቹ 2030 የረሃብን ደረጃ ዜሮ ለማድረስ በሚያስችል መንገድ ላይ እንዳልሆነች ዓለም አቀፉ የምግብ እና እርሻ ድርጅት (ፋኦ) የአፍሪካ ተወካይ አበበ ሀይለ ገብርኤል ገለፁ።

በአህጉሪቱ ረሃብን ለማጥፋት የተያዘው ግብ በርካታ ስድራዎች እንደሚቀሩት አፍሪካ በዘርፉ ያከናወነችው ስራ በተገመገመበት ወቅት ተገልጿል።

ረሃብን ከአፍሪካ ለማጥፋት የተከናወነው ስራ የሚያረካ አይደለም ያሉት አቶ አበበ ሀይለ ገብርኤል ከአየረ ንብረት ለውጥ ፣ ከዝቅተኛ የኢኮኖሚ ሁኔታ ፣ ከኮቪድ19 ተፅዕኖ እና ከኢንቨስትመንት ጋር በተያያዘ አሁንም ተግዳሮቶች እንዳሉ ተናግረዋል።

ነገር ግን የአፍሪካ አህጉራዊ የንግድ ቀጠና የአህጉሪቱን የምግብ ስርዓት ለማሸጋገር ለየት ያለ አጋጣሚ እንዳለውም ጠቁመዋል።

በአፍሪካ ረሃብን ለማጥፋት ፖለቲካዊ ፈቃደኝነት እና በከፍተኛ ሁኔታ መነሳሳት መኖሩ ቁልፍ ጉዳይ እንደሆነም አብራርተዋል።

ከዚህ ባለፈም በብሄራዊ እና አካባቢያዊ  ደረጃ እርምጃዎች እና ኢንቨስትመንት ወሳኝ እንደሆኑም ነው የተገለፀው።

የዓለም ምግብ ድርጅት ተወካይ ክሪስ ቶይ በበኩላቸው ረሃብን ለማጥፋት እና የምግብ እጥረትን ለመቅረፍ የአፍሪካ ሀገራት በገጠር ኢንቨስትመንትን ማሳደግና ቀጣይነት ያለው የመሰረተ ልማት ግንባታ እና የሰው ሀይል ልማት ላይ ሊሰሩ ይገባል ብለዋል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.