Fana: At a Speed of Life!

ኢራን በእስራኤል ላይ የአፀፋ እርምጃ እወስዳለሁ ስትል አስጠነቀቀች

አዲስ አበባ ፣ ሚያዝያ 4፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ˝እስራኤል በኢራን የኒውክሌር ጣቢያ ላይ ጥቃት መፈፀሟን ተከትሎ˝ የበቀል እርምጃ እንደምትወስድ አስታወቀች።

የኢራን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ባወጣው መግለጫ በወሳኝ የኒውክሌር ጣቢያ ላይ በቅርቡ ለተፈፀመው ጥቃት እስራኤልን ተጠያቂ አድርጓል።

የኢራን ባለስልጣናት የኒውክሌር ሽብርተኝነት ብለው የገለፁት ጥቃት በናታንዝ ዩራኒየም ማበልፀጊያ ላይ የሀይል መቋረጥ ማስከተሉ ተነግሯል።

በዚህ የኒውክሌር ጣቢያ ላይ ኢራን ዘመናዊ የዩራኒየም ማበልፀጊያ ስራ ማስጀመሯን ነው ቢቢሲ የዘገበው።

እስራኤል በጉዳይ ዙሪያ አስተያየት ባትሰጥም በእስራኤል የሚገኝ የሬዲዮ ጣቢያ በሞሳድ የተፈፀመ የመረጃ መረብ ጥቃት መሆኑን የደህንነት መረጃ ምንጮቹን ዋቢ በማድረግ  ዘግቧል።

ጄሩሳሌም ፖስት ባወጣው ዘገባም  ጥቃቱ የኒውክሌር ማበልፀጊያው ውስጣዊ የሀይል ስርዓት ለማውደም  ማስቻሉን  ኒውዮርክ

ታይምስ ጠቅሶ ዘግቧል።

በዘገባው ጥቃቱ በናታንዝ ዩራኒየም ማበልፀጊያ ላይ ከፍተኛ ጉዳት ማስከቱ የተገለፀ ሲሆን የኒውክሌር ጣቢያው በድጋሜ ወደ ስራ ለመመለስ በትንሹ ዘጠኝ ወራት ያስፈልገዋል ተብሏል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.