Fana: At a Speed of Life!

ኢትዮ ቴሌኮም የሞጁላር መረጃ ማዕከልን በጋራ ለመጠቀም የሚያስችል ሥምምነት ከ5 ተቋማት ጋር ተፈራራመ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 12፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮ ቴሌኮም የሞጁላር መረጃ ማዕከልን በጋራ ለመጠቀም የሚያስችል ሥምምነት ከተለያዩ የፋይናንስ ተቋማት ጋር ተፈራረመ።

ተቋሙ ሥምምነቱን የተፈራረመው ከዘመን፣ ዘምዘምና ሂጅራ ባንኮች እንዲሁም ሬስ ማይክሮ ፋይናስና ከዌብስክሪብስ የፋይናንስ ተቋማት ጋር ነው።

የተቋሙ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ፍሬህይወት ታምሩ እንደተናገሩት፥ በኢትዮጵያ ዲጂታል ኢኮኖሚ ለመገንባት እንደ ዳታ ማዕከል ዓይነት አሰራር መዘርጋት ወሳኝ ነው።

የመረጃ ማዕከሉን በጋራ ለመጠቀም ሥምምነት የገቡ ተቋማት የአገልግሎት አሰጣጥ አቅም ከማሳደግ ባለፈ ጥራትን የሚጨምር መሆኑን አብራርተዋል።

በአሁኑ ወቅት በፋይናንስ ዘርፍ የአገልግሎት ተጠቃሚ ቁጥር እየጨመረ መሆኑን ጠቁመው ፍላጎቱን በዘመናዊ ቴክኖሎጂ መመለስ ይገባል ብለዋል።

ኢትዮ-ቴሌኮም ባለፉት ጥቂት ዓመታት አዳዲስ አሰራር እየዘረጋ መሆኑን ጠቅሰው ወደ ፊትም አጠናክሮ እንደሚቀጥል መናገራቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.