Fana: At a Speed of Life!

ኢትዮጵያ በ6ኛው የዓለም የጉምሩክ ድርጅት ልዩ መብት የተፈቀደላቸው የኢኮኖሚ አንቀሳቃሾች ኮንፈረንስ ላይ እየተሳተፈች ነው

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 30፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የጉምሩክ ኮሚሽን ኮሚሽነር ደበሌ ቃበታን ጨምሮ ሌሎች የኮሚሽኑ አመራሮች በቻይና-ሼንዘን እየተካሄ በሚገኘው 6ኛው የዓለም የጉምሩክ ድርጅት ልዩ መብት የተፈቀደላቸው የኢኮኖሚ አንቀሳቃሾች ዓለም አቀፍ ኮንፈረንስ ላይ እየተሳተፉ ነው፡፡

በኮንፈረንሱ ላይ ሴቶችን በዓለም አቀፍ ንግድ የማብቃት እና ቴክኖሎጂን ለዓለም አቀፍ ንግድ ስጋት ስራ አመራር ጥቅም ላይ ማዋልን የተመለከቱ ጉዳዮች ላይ እንደሚመክር ተገልጿል፡፡

ከኮንፈረንሱ ጎን ለጎንም ልዩ መብት ስለተፈቀደላቸው የኢኮኖሚ አንቀሳቃሾች ግንዛቤን መፍጠር የሚያስችል እና ትስስርን የሚያጠናክር ዐውደ-ርዕይ እየተካሄደ መሆኑን የኮሚሽኑ መረጃ አመላክቷል፡፡

የኢትዮጵ ጉምሩክ ኮሚሽን ልዩ መብት የተፈቀደላቸው የኢኮኖሚ አንቀሳቃሾች ፕሮግራምን ተግባራዊ እያደረገ መሆኑም ነው የተጠቀሰው፡፡

በሀገር ውስጥ ታክስ እና በሌሎች የሀገሪቱ ሕጎች ታማኝ ስለመሆናቸው በኦዲት የተረጋገጠላቸው 199 ድርጅቶችን በመለየት በዝቅተኛ የስጋት ደረጃ እንዲስተናገዱ እንዲሁም ፈጣን እና የቅድሚያ አገልግሎት እንዲያገኙ እየተደረገ ነውም ተብሏል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.